top of page

የኢትዮጵያዊያን የቆየ የጋራ አብሮነት እሴቶች እንደ ቡና መጠራራት፣ እድርና ማህበር ያሉ ማህበራዊ ትስስሮች ወንጀልን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ተባለ።

  • Mar 25
  • 1 min read

መጋቢት 16/2018

 

የኢትዮጵያዊያን የቆየ የጋራ አብሮነት እሴቶች እንደ ቡና መጠራራት፣ እድርና ማህበር ያሉ ማህበራዊ ትስስሮች ወንጀልን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ተባለ።

 

እነዚህ ማህበራዊ ቅርርቦሾች በሚላሉበት ወቅት ደግሞ ወንጀል በተደጋጋሚ የመከሰት ዕድሉ ሰፊ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

 

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ወንጀል የስነ ልቦና መምህሩ ዋና ኢንስፔክተር ጉግሳ ገብረግዚአብሔር  አንድ ማህበረሰብ ጠንካራ የጋራ እሴቶች ሲኖሩት ወንጀልን የመቆጣጠር አቅሙ ይጨምራል ብለዋል። 

 

በአንድ አካባቢ የሚኖር ማህበረሰብ  ወንጀል እንዳይፈጠር፣ ስርቆት እንዳይኖር፣ ግድያን እንዳይከሰት፣ ከማህበረሰቡ እሳቤ ያፈነገጠ ባህሪም እንዳይኖር የሚቆጣጠርበት ስልት ማህበራዊ ቅርርቦሹን ማጠናከር ነው የሚሉት ወ/ኢ/ር ጉግሳ ቡና ተጠራርቶ በጋራ መጠጣት፣ ማህበርና እድር ደግሞ የማህበረሰቡን መቀራረብና አብሮነት እንደሚያድጉ ተናግረዋል።

 

ዓይነቱ ዘዴ በአብዛኛው በገጠሪቱ አካባቢ ጥቅም ላይ እንደሚውልም ዋ/ኢሩ አስታውሰዋል፡፡

 

በተጨማሪም ያጠፋ የሚቀጣበት፣ ተበዳይ የሚካስበት ባህላዊ የሽምግልና ሥርዓት  መቅረት የሌለበት ወንጀልን ለመቀነስ ዓይነተኛ መሳሪያ እንደሆነም የስነ ወንጅል አስተማሪው መክረዋል፡፡

 

ወንጀልን ለመቆጣጠር በቴክኖሎጂና በፖሊስ ብቻ እንደማይሆን የጠቀሱት አስተማሪው ማህበረሰባዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር ፣ ጎረቤት ለጎረቤት መጠባበቅና የቆዩ ባህላዊ እሴቶችን ለዘመኑ ወንጀል መከላከያ ስልት እንዲሆኑ አላምዶ መጠቀም ዋነኛው መፍትሄ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ጉግሳ ገብረግዚአብሔር አሳስበዋል።

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

ገዛ ጌታሁን

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

Recent Posts

See All
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ።

ሐምሌ 20 2018 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ። እቅዱ የኔትወርክ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ፣ የሰብስቴሽን እና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ ስማርት ግሪድ እና ቆጣሪ ማስፋፋትን እንደሚያካትት አገልግሎቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page