top of page

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ሼባ ማይልስ እና አኮያ ፕሮፐርቲስ አብሮ ለመስራት ስምምነት መፈራረማቸው ተሰማ።

  • sheger1021fm
  • 13 minutes ago
  • 1 min read

ታህሳስ 8/2018


የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ሼባ ማይልስ እና አኮያ ፕሮፐርቲስ አብሮ ለመስራት ስምምነት መፈራረማቸው ተሰማ።


በስምምነቱ መሰረት ከአኮያ ፕሮፐርቲስ መኖሪያ ቤቶችን እና የንግድ ሱቆችን የሚገዙ ደንበኞች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይልስ የጎልድ አባልነት ሽልማት በክብር እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል።


ይህም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና የሪል ስቴት ዘርፍ መካከል ያለውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ተብሎ አንደታመነበት ከተላከልን መግለጫ ላይ ተጠቅሷል፡፡

ree

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ ጋር አብሮ ለመስራት መፈራረሙ የተነገረው አኮያ ፕሮፐርቲስ በሪል ስቴት፣በቡና ምርትና ኤክስፖርት እንዲሁም በተሽከርካሪ ግብይት የተሰማራ አና ከ230 በላይ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረ መሆኑ ተነግሯል፡፡


ኩባንያው ተዋናይ እፀህይወት አበበን የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር ማድረጉንም ሰምተናል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page