የኢትዮዽያን የቴሌኮም ኢንዱስትሪ ሁለተኛ አቅራቢ ሆኖ የተቀላቀለው ሳፋሪኮም ኢትዮዽያ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉ ተሰማ።
- sheger1021fm
- 26 minutes ago
- 1 min read
ታህሳስ 15/2018
የኢትዮዽያን የቴሌኮም ኢንዱስትሪ ሁለተኛ አቅራቢ ሆኖ የተቀላቀለው ሳፋሪኮም ኢትዮዽያ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉ ተሰማ።
ሳፊሪኮም ኢትዮዽያ ለደንበኞቹ የዋጋ ማሻሻያ ወይም የአገልግሎት ጭማሪ ማድረጉንም ከኦፕሬተሩ ሰምተናል።
ጭማሪ ተደርጎበታል የተባለው የዳታ ጥቅል አገልግሎት ላይ ነው።
ሳፋሪኮም ኢትዮዽያ ይህንን ጭማሪ ያደረገው የኢንቨስትመንት እና የኦፕሬሽናል ወጪዎች ከፍ ማለታቸውን ተከትሎ እንደሆነ ሰምተናል።
ኩባንያው ለጊዜው ጭማሪ ያደረገበት የዳታ ጥቅል አገልግሎት ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ አልጠቀሰም።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ኢንተርኔት እያቀረበ ያለው ካወጣው ዋጋ ከእጥፍ በላይ እየቀነሰ ወይም እየከሰረ መሆኑንን መናገሩ ይታወሳል፡፡

ኩባንያው ስራውን እያስፋፋ፣ አገልግሎቱን እያቀረበ ያለውም በባለ አክሲዮኖቼ ድጋፍ ነው ብሎ ነበር፡፡
የኮሙኒኬሽን ባለስልጣን የሞባይል ኢንተርኔት ዋጋን ተመልክቶ አዲስ ተመን እንደሚያወጣ እንጠብቃለን ፣ ያ ካልሆነ ግን የቴሌኮም ዘርፍ ባለበት ይቆማል የሚል ስጋት አንዳለሁ ኩባንያው ከወራት በፊት መናገሩ ይታወሳል፡፡
ሳፋሪኮም ኢትዮዽያ በሐገር ቤት የቴሌኮም ገበያ ለውድድር ክፍት መሆኑን ተከትሎ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ሶስት አመት አሰቆጥሯል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኬንያው ሳፋሪኮም ለሚመራ "ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ" የተሰኘ ጥምረት አካል ነው፡፡
ጥምረቱ የኬንያው ሳፋሪኮም ፤ የዩናይትድ ኪንግደም ቮዳፎን እና ቢአይአይ ግሩፕ፣ የአለም ባንኩ አይ ኤፍ ሲ፣ የደቡብ አፍሪካ ቮዳኮም፣ የጃፓኑ ሱሚቶሞ ያቀፈ ነው።
ጥምረቱም ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በደረሰው ስምምነት መሠረት ጨረታ ያሸነፈበትን 850 ሚሊዮን ዶላር ለመንግሥት ከፍሎ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በድሬዳዋ ከተማ የጀመረው በነሃሴ ወር 2014 ዓ.ም ነበር፡፡
ኩባንያው የደንበኞቼ ቁጥር 12 ሚሊዮን በላይ ደርሷል፣ ይህም ከፍተኛ ስኬት ነው መለቱ ይታወሳል፡፡
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1








