top of page

በኢትዮጵያ የአሉሚኒየም ምርቶች ላይ የተሰማራው ''ቴክሃፍ አሉሚኒየም'' አለም አቀፍ የጥራት መስፈርቶችን በማሟላት እውቅና ማግኘቱ ተነገረ

  • Apr 30
  • 1 min read

ሚያዝያ 22/2018


በኢትዮጵያ ለአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ የሃይል ማመንጫዎች፣ኢንደስትሪ ፓርኮችና ሌሎችም ግዙፍ የግንባታ ስራዎች የሚውሉ የአሉሚኒየም ምርቶች ላይ የተሰማራው ቴክሃፍ አሉሚኒየም የተባለ ተቋም አለም አቀፍ የጥራት መስፈርቶችን በማሟላት እውቅና ማግኘቱ ተነገረ፡፡


ተቋሙ በቅርቡ ወደ አለም አቀፍ ገበያ እንደሚቀላቀለም ጠቅሷል፡፡


ቴክሃፍ አሉሚኒየም አራት ዓለም አቀፍ የጥራት ምስክር ወረቀቶችን ማግኘቱ የተነገረ ሲሆን እውቅናዎቹ በኢትዮጵያ የተሰሩ ምርቶች በዓለማቀፍ ገበያ ገብተው እንዲወዳደሩ ለማድረግ በር የሚከፍት ነው ተብሏል፡፡


በዓለም ላይ የአሉሚኒም ምርቱ ካለው የምርት እድገት አንጻር የኢትዮጵያ ዝቅተኛ መሆኑን የሚያነሱት የቴክሃፍ አሉሚኒየም የሽያጭ ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ ጌታሁን ጥላሁን ተቋማቸው ይህንን ክፍተት ለማጥበብና የኢትዮጵያ ምርት ከአለም ገበያ ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚሰራ ነው ብለዋል፡፡


ለአሉሚኒየም ምርት የሚሆኑ አብዛኛዎቹ ግብዓቶች ከውጭ እንደሚገቡ የሚጠቅሱት አቶ ጌታሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆንና ምርቶችንም ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የጥሬ እቃ ማምረቻውንም መሳሪያ ጭምር ቴክሃፍ አሉሚኒየም በሀገር ውስጥ እየተከለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


ኢትዮጵያ በአሉሚኒየም ምርት ከሌሎች ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ እንድትሆን የተለያዩ አማራጮች እየተጠቀምን ነው የሚሉት የቴክሃፍ አሉሚኒም የሽያጭ ክፍል ሃላፊው ለዚህም አለማቀፍ የጥራት መመዘኛዎችን ማሟላትና ዘመናዊ የምርት ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እየሰራ ነው ብለዋል፡፡


ቴክሃፍ አሉሚኒም በ4 ቢልየን ብር መነሻ ካፒታል በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ አካባቢ የተገነባ ሲሆን በዓመት ከ15ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ በቀን ደግሞ ከአርባ አምስት ቶን በላይ አሉሚኒየም የሚያመርት ፋብሪካ ነው፡፡


ፋብሪካው በመጪዎቹ ስድስት ወራት የማምረት አቅሙን በእጥፍ በማሳደግ ወደተለያዩ ሀገራት የአሉሚኒየም ምርቶችን ኤክስፖርት ለማድረግ የማስፋፊያ ስራ እየከወነ መሆኑም ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡

ሰኔ 15/2018 የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡ በእዚሁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ግማሽ ያህል ሰራተኞቹን መቀነሱን እና የሰረዘው ፕሮጅክትም መኖሩን መናገ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page