ለመጪው ሀገራዊ ምርጫ ለመራጭነት ካርድ የወሰዱ አካል ጉዳተኞች ከእቅዱ 3 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ተናገረ፡፡
- 3 hours ago
- 1 min read
ሚያዝያ 22/2018
ለመጪው ሀገራዊ ምርጫ ለመራጭነት ካርድ የወሰዱ አካል ጉዳተኞች ከእቅዱ 3 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ተናገረ፡፡
አካል ጉዳተኞች አጠቃላይ ከማህበረሰቡ ከ17 በመቶ በላይ መሆናቸው ይነገራል፡፡
ከመካከላቸው 5 ሚሊየኑ የምርጫ ካርድ ይወስዳሉ ተብሎ ቢጠበቅም የወሰዱት ግን 167,000 ብቻ ናቸው ሲል ፌዴሬሽኑ ነግሮናል።

የምርጫ ካርድ የወሰዱ አካል ጉዳተኞች ቁጥር ዝቅተኛ የሆነበት የመረጃ ክፍተት ምክንያት አንዱ እንደሆነም ተነግሯል።
ይህን የነገሩን የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ጉጆ አብዛኛው አካል ጉዳተኛ የምርጫ ካርድ አለመውሰድ ጋር በተያያዘ ቅሬታችንን ለምርጫ ቦርድ አቅርበናል፤ እንደ ሃሳብ ያቀረብነውም የመራጮች ምዝገባ እንዲራዘም የሚል ነበር ነገር ግን በምርጫ ቦርድ በኩል ተቀባይነት አላገኘንም ብለዋል።
በሌላ በኩል ለተመራጭነት የቀረቡ እጩ አካል ጉዳተኞች ቁጥር ደግሞ ከባለፈው የምርጫ ዘመን አንፃር ከፍተኛ እንደሆነም ሰምተናል።
በ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ከ250 በላይ አካል ጉዳተኞች ለመመረጥ እንደተመዘገቡ የፌዴሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ነግረውናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7




Comments