የአፍሪካ ቀን
- 46 minutes ago
- 2 min read
ግንቦት 18/2018
አፍሪካ በምዕራባውያን ሚዲያ የግጭትና የረሃብ ቀጠና ተደርጋ በመሳሏ ምክንያት ለኢንቨስትመት አመቺ ካልሆኑ አህጉራት መካከል በመሆኗ በየዓመቱ 4.2ቢሊዮን ዶላር እንደምታጣ ጥናት አሳየ፡፡
በየዓመቱ ግንቦት 17 የአፍሪካ ቀን የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት) እ.ኤ.አ በ1963 በዚህ ቀን መመስረቱን ተከትሎ የአፍሪካ ቀን ተብሎ ይከበራል።
የዘንድሮውን የአፍሪካ ቀን Africa no filter የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት "አፍሪካ እየጠበቀች አይደለም"የሚል የሚዲያ ዘመቻ በማስጀመር 63ኛውን የአፍሪካ ቀን በትላንትናው እለት አክብሯል፡፡
አፍሪካ በምዕራባውያን ሚዲያ ለዘመናት የረሃብና የሰቆቃ ምልክት ተደርጋ ስትገለፅ ቆይታለች ያሉን የአፍሪካ ኖ ፊልተር ዋና ዳይሬክተር ሞኪ ማኩራ ናቸው፡፡
ድርጅታቸው አፍሪካ የተጣለባትን የጠለሸ ስም በትክክለኛ መልኳ ለመከየር እንደሚሰራና ላለፉት 6 ዓመታት የውትወታና የጥናትና ምርምር ስራዎችን ሲሰራ እንደነበር ዳይሬክተሯ ነግረውናል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ ሞኪ ማኩራ እንደሚሉት Africa no filter ባደገው ጥናት አፍሪካ ምዕራባውያን በሚዘውሯቸው ሚዲያዎች በተሰጣት ስም ምክንያት ለኢንቨስትመት ከማይመረጡ አህጉራት ቀዳሚዋ ሆናለች፤በዚህም ምክንያት በየዓመቱ 4.2 ቢሊዮን ዶላር እያጣች ነው ብለውናል፡፡
"አፍሪካ እየጠበቀች አይደለም" የተሰኘውና በትላንትናው እለት የተጀመረው የሚዲያ ዘመቻ አፍሪካ ማንንም ሳትጠብቅ፤የምንም ልገሳ ሳያስፈልጋት በራሷ መቆም የምትችል አህጉር እንደሆነችና እስካሁን ስለ አፍሪካ ሲነገር የቆየው ትክክለኛ ማንነቷ አለመሆኑን ለማሳየት ያለመ ነው ተብሏል፡፡
ዘመቻው ለ3ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በየወሩ በ25ተኛው ቀን የሚቀጥል፤በተለይ ወጣቶች በያዙት የሚዲያ አማራጭ አሁን ያለውን የአፍሪካ ትክክለኛ ገጽታ እንዲያሳዩ ድርጅቱ አፍሪካ ኖፊለተር በገንዘብና በሃሳብ እንደሚደግፋቸው ዋና ዳይሬክተሯ ሞኪ ማኩራ ነግራናል፡፡
በጌትስ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ ይህንን ስራ እንደተ ጀመረ የነገሩን ሃላፊዋ ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት በየወሩ የሚሰራው አስተሳሰብን የማስቀየር ስራ በመላው አፍሪካ የሚሰራ መሆንና በተለይ እንደ ፊልም ባሉ የኪነጥበብ ስራዎችም መልዕክቶቹ እንደሚስተጋቡ ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ……
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ……
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/YouTube : https://shorturl.at/18TS1Telegram : https://shorturl.at/68aeKFacebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRxX :- https://x.com/shegerfm?s=2LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6iTiktok : https://shorturl.at/lhYivInstagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments