“የድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና” በኢትዮጵያ ቀዳሚው ነፃ የንግድ ቀጠና ነው።
- 1 hour ago
- 1 min read
ግንቦት 18/2018
“የድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና” በኢትዮጵያ ቀዳሚው ነፃ የንግድ ቀጠና ነው።
2014 መጨረሻ ላይ ስራ የጀመረው ይህ ነፃ የንግድ ቀጠና ለጅቡቲ ወደብ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ከሁለት ዓመት በፊት የተቋቋመውና በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ የሚገኘው ገዳ ነፃ የንግድ ቀጠና ደግሞ ሁለተኛው ነው፡፡
እነዚህ ነፃ የንግድ ቀጠናዎች በውስጣቸው መካሄድ በሚቻል ሰፋ ያሉ የኢኮኖሚ ተግባራት ከልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እንደሚለዩ ይጠቀሳል፡፡
በነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ ምርት ማምረት ፤ ንግድ ማካሄድ እና የሎጅስቲክስ አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል፤በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጳውሎስ በለጠ ነግረውናል፡፡
የፋይናንስ እና ሆቴል አገልግሎቶችም ማቅረብ ይቻላል ብለዋል፡፡
ነጻየንግድ ቀጠናዎቹ የተቋቋሙት የጉሙሩክ እና የፋይናንስ ሥርዓቱን በማቅለል በቀላሉ ምርቶችን ከወደብ ለማስገባት እንደሆነም አቶ ጳውሎስ ነግረውናል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር በነፃ የንግድ ቀጠና የሚሰሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ የሚያደግ መመሪያ ማውጣቱን ሠምተናል፡፡
መመሪያው ባለሃብቶቹ የቱንም ያህል ቢያተርፉ ግብር የገቢ ግብር እንዳይከፍሉ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡
በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ገብተው ለሚሰሩ ባለሃብቶችም ማበረታቻዎች እንደሚሰጡ ያስታወሱት አቶ ጳውሎስ ፤ በነጻ ንግድ ቀጠና ውስጥ ለሚሰሩት አሁን የተደረገው ከዚያ በተጨማሪ እንደሆነ ነግረውናል፡፡
የተደረገው ማበረታ ሰዎች ተጨማሪ ሃብት እንዲያፈሩ ፤ የሀገር ኢኮኖሚም እንዲያደግ ያግዛል ተብሏል፡፡
ገንዘብ ሚኒስቴር ያወጣው አዲሱ መመሪያ የሚመለከተው በነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚሰሩ ነጋዴዎችን ፤ የተለያዩ የንግድ ግብአቶችን በማቅረብ እና በመሸጥ ሂደት ያሉ ተዋናዮችን እና የሀገሪቱን የንግድ ትስስር ለማሳደግ የሚጥሩ ባለሃብቶችን ነው ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ……





Comments