top of page

አሁን በስራ ላይ ያሉ ሁሉም አሽከርካሪዎች ሰልጥነው የብቃት ምዘና አንዲወስዱ የሚያስገድድ ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓት ሊዘረጋ ነው፡፡

  • 48 minutes ago
  • 1 min read

ግንቦት 18/2018



አሁን በስራ ላይ ያሉ ሁሉም አሽከርካሪዎች ሰልጥነው የብቃት ምዘና አንዲወስዱ የሚያስገድድ ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓት ሊዘረጋ ነው፡፡

ሁሉም አሽከርካሪዎች እንደገና እንዲሰለጥኑና እንዲመዘኑ በማድረግ ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችል አጠቃላይ የሰነድ ዝግጅት ተጠናቋል ያለው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ነው፡፡


ይህ አዲስ አሰራር ከተለመደው አሰራር በተለየ መልኩ ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፣ የምዘና ሂደቱ በዲጂታል ሲስተም እንዲመራ ተደርጎ ተቀርጿል ሲል ሚኒስቴር መ/ቤቱ መባህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መገለጫ ላይ ጠቅሷል ።


አሽከርካሪዎች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ቅድሚያ ስልጠና ይወስዳሉ ተብሏል ።

በዚሁ መሰረት ይህንን ሀገራዊ ፕሮጀክት በይፋ ወደ ትግበራ ለማስገባት በተለይም አጠቃላይ የአሽከርካሪዎች ምዝገባ እና ስልጠና በተመለከተ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከኤስ ዲ ኤስ ሴፍቲ ኤንድ ድራይቪንግ ስኪልስ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የስራ ውል ስምምነት መፈረማቸው ተሰምቷል።


በመሆኑም ይህ "ሀገር አቀፍ የአሽከርካሪዎች የብቃት ምዘና፣ የስልጠና እና የደህንነት ማሻሻያ ፕሮጀክት" የመንገድ የትራፊክ ደህንነትን በማጠናከር ረገድ የጎላ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ተገምቷል፡፡


ማናቸውም አሽከርካሪዎች በሙሉ አዲሱን የብቃት ምዘና በመውሰድ እና በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ብቃታቸውን በተጨባጭ በማረጋገጥ ብቻ እንዲያሽከረክሩ የሚያስገድድ ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓት ይዘረጋል ተብሏል።


ይህ አሰራር የመንገድ ደህንነትን በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ዜጎቻችን ብሎም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በመንገድ የትራፊክ አደጋ ምክንያት ሞትና የአካል ጉዳት እንዲሁም የንብረት ውድመት ለመቀነስ ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑ ከፍተኛ እምነት ተጥሎበታል።


በመሆኑም ሁሉም አሽከርካሪ በዚህ ሂደት የሚያልፍ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይም ለዚህ ዙር በቅድሚያ ማንኛውም የንግድ ተሽከርካሪ የሚያሽከረክር አሽከርካሪ የምዝገባና የስልጠና እንዲሁም የምዘና ሂደቱ በቅርቡ ስለሚጀመር ሁሉም ዝግጁ እንዲሆን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አሳስቧል።



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…











Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page