የአፈርን ለምነትና ጤናማነት በመጨመር የተሻለ ምርት እንዲገኝ የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች ስራ ላይ እየዋሉ ነው ተባለ ፡፡
- 33 minutes ago
- 1 min read
የካቲት 11/2018
የአፈርን ለምነትና ጤናማነት በመጨመር የተሻለ ምርት እንዲገኝ የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች ስራ ላይ እየዋሉ ነው ተባለ ፡፡
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ እየተተገበረ ያለው ይህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እየተራቆተ እና ምርት እየራቀው የመጣውን ለግብርና የሚውል መሬት ለምነት ለመመለስ ያግዛል ተብሏል፡፡
ይህ ባዮቻር የተባለው ቴክኖሎጂ እየተራቆተ የመጣውን የእርሻ መሬት ለማከም እንደሚረዳ የነገሩን በጅማ ዩንቨርስቲ ግብርናና የእንስሳት ህክምና ኮሌጅ ውስጥ መምህርና ተመራማሪ እንዲሁም የአፈር ለምነት ለማስጠበቅ የተለያዩ ጥናቶችን ያደረጉት ዶ/ር ሚልክያስ አህመድ ናቸው፡፡
የእርሻ መሬት ከጊዜ ወደ ጊዜ የተፈጥሮ ማዳበሪያን በመጠቀም እንኳን የሚፈልገውን ያክል ምርት መስጠት እየቻለ አይደለም የሚሉት ዶ/ር ሚልክያስ ይህ ዓይነቱ ቴክኖሎጂ የተሻለ ምርት ለማግኘት ያግዛል ብለዋል፡፡
ይህንን ምክንያት በማድረግ ሃገር በቀል መፍትሄዎች በሀገሬው ልጆች መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ በአካባቢ ከሚገኙ ተረፈ ምርቶች ባዮቻርን በማዘጋጀት ለአካባቢው አርሶ አደሮች እየተሰጠ እንደሆነም ነግውናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7








