የቡና ዓይነቶች ጣዕም፣ የቀለም እና የዋጋ ልዩነታቸው ታዲያ ከየት መጣ?
- 12 minutes ago
- 2 min read
የካቲት 11/2018
ኢትዮጵያ የከፋ፣ የጅማ፣ የሀረር እና ይርጋ ጨፌ የቡና ዝርያዎች መገኛ ሀገር ናት፡፡
እነዚህ የቡና ዓይነቶች መነሻቸው አንድ ፤ ዝርያቸውም ተመሳሳይ፣ መሆኑን የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡
የጣዕም፣ የቀለም እና የዋጋ ልዩነታቸው ታዲያ ከየት መጣ?
ተመራማሪዎች በማስረጃ፣ የታሪክ ምሁራን በቅርስ፣ አርኪ ኦሎጂስቶችም በመሬት ውስጥ ምስክርነት ሌላውም ሌላውም አለኝ ያለውን ማስረጃ በማቅረብ ኢትዮጵያ ቡናን ለአለም ያስተዋወቀች ምድር ስለመሆኗ ይሞግታሉ።
የቡና ርስት ኢትዮጵያ ስለመሆኗ ሳይንስም፣ ታሪክም፣ ቢያረጋግጥም፣ መጠሪያው 'ኮፊ አረቢካ' መሰኘቱን ብዙዎች በቁጭት ይናገሩታል፡፡
“ኮፊ አረቢካ” የሚለዉን ስያሜ ያገኘው የቀደምት የአረብ ነጋዴዎች ከኢትዮጵያ ወስደው በራሳቸው ስም ሰጥተው መጠሪያው እንዳደረጉት ታሪክ ጠቅሰው ፣ ማስረጃ አቅረበው የሚናገሩ አሉ፡፡
ያም ሆነ ይህ የቡና እትብት የኢትጵያ ምድር ስለመሆኑ እርግጥ ነው ይላሉ ለ37 ዓመት ጥናት ያደረጉት አቶ ሰለሞን ተክሌ።

የታሪክ አስተማሪው አቶ አሰፋ ገብረማሪም ደግሞ ኢትዮጵያዊነትና ቡና የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው።
ቡና በኢትዮጵያዊን ማህበራዊ ህይወት ውስጥ ያለው ፋይዳ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ በላይ ገዝፎ ይታያል ይላሉ፡፡
በቡና መገኛዋ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የጅማ፣ የሐረር፣ የከፋ፣ የይርጋ ጨፌ ሌላም ሌላም መጠሪያ ይዘው የሚታወቁት የቡና ዓይነቶች ፣ ስለምን በጣዕም፣ በቀለምና በዋጋ መለያየት ከአፈሩ ፣ ከሚደረግለት እንክብካቤ፣ ከአየር ፀባዩና በሌሎች ምክንያት እንደሆነ ተመራማሪው ሰለሞን ተክሌን ይጠቁማሉ፡፡
ቡና የኢትዮጵያ ለዓለም የሰጠችው ስጦታ ነው።
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ኑሯቸው ከቡና ጋር በቀጥታ የተቆራኘ ነው።
የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ በማስገኘትም የቡና ስም ጎልቶ ይጠራል፡፡
ቡና ዝርያው አንድ ቢሆንም፣ ምድሪቱ በቸርነቷ ያደለችው የተለያየ መዓዛ ግን ለዓለም ገበያ ልዩ ድምቀት ሆኗል።
ዛሬም ድረስ በየቤቱ የሚጤሰው የቡና ጪስ የፍቅር፣ የአንድነትና የጽናት ምልክት ሆኖ ቀጥሏል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ገዛ ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7








