top of page

ሰራተኛ ቀጥረው የሚያስጠብቁ የግል ኤጅንሲዎች

  • 2 hours ago
  • 1 min read

የካቲት 11/2018


በአዲስ አበባ ባንኮችን፣ የግል ተቋማትን፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ሌላም ሌላም እንዲጠብቁ ሀላፊነት ወስደው፣ ህጋዊ ፍቃድ ተቀብለው፣ ሰራተኛ ቀጥረው የሚያስጠብቁ የግል ኤጅንሲዎች ቁጥር 250 ደርሷል ተብሏል።


በእነዚህ ኤጀንሲዎች ስር ተቀጥረው ዩኒፎርም ለብሰው፣ ዱላ ታጥቀው የሚጠብቁት የመስሪ ቤቱ ንብረት እንዳይዘረፍ፣ ተቋሙ ጥቃት እንዳይደርስበት በር ላይ ቁመው የሚቆጣጠሩ፣ ሰራተኛው ሲገባ ፍትሸው የሚያስገቡ፣ ሲወጣ አይተው የሚሸኙ ካላቸው ሀላፊነት ከተሰጣቸው የስራ ድርሻ አንጻር የሚከፈላቸው ደመወዝ ለእለት ጉርስ የሚበቃ እንዳልሆነ ይጠቀሳል።


ብዙዎቹ በየቀኑ በሚሊዮን ሚቆጠር ብር ሲገባ ሲወጣ የሚውልበትን ባንክ እየጠበቅን የምንቀበለው ክፍያ ለቤት ኪራይ የመክፈል አቅም ያለው አይደለም፡፡

ደግሞም ኤጅንሲዎች ከተቋሙ የሚቀበሉት ብር ብዙ ቢሆንም ለእኛ የሚደርሰን ግን እጅግ ያነሰ ነው ሲሉ ኤጀኒሲዎችን ይኮንናሉ።


ኤጀንሲዎች በበኩላቸው ሰራተኞች ደሞዝ ያንሳል ቢሉም ችግሩ የሚዋዋሉት ተቋም ለኤጅንሲው ሚከፍለው ገንዘብ አነስተኛ በመሆኑ ነው ይላሉ።


አቶ በላይ ተሰማ ይባላሉ በአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ የስራ ስምሪት ፍቃድ ቁጥጥር ቡድን መሪ ናቸዉ።


እሳቸው በእርግጥም እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎች እንደሚደጋጥሙ ጠቅሰው ችግሮችን ለመፍታት የተቋሙንና የኤጀንሲዎን የውል ስምምነት በማረጋገጥ እንደሚፈቱ ነግረውናል።


20 80 አከፋፈል ኤጅንሲዎች በፍርድ ቤት አሳግደዉታል ያሉን አቶ በላይ ተሰማ ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ችግር ሲፈጠር ምንም ኤጀንሲውን ደሞዝ ጨምር የምንልበት ህጋዊ ስልጣን ባኖረንም ቢያንስ 60 በሞቶና 70 በመቶ አንዲከፍል እንደሚያደርጉ ሀላፊው ጠቁዋል።


በ2018 ባሳለፍነው ስድስት ወራት በተደረገ ቁጥጥር ከ70 በላይ የሚሆኑ ኤጄንሲዎች ለፍቃድ ሲሰሩ ስለመገነታቸዉ አስታዉሰዋል።


ባለፉት ስድስት ወራትም ባሳዩት የስነ ምግባር ጉድለት 5 ኤጄንሲዎች ታግደዋል ብለዋል።


አሁንም ከሰራተኛ መብት ጋር ችግር የሚፈጥሩ ድርጅቶችን ከማገድ አስከ ፍቃድ መንጠቅና በህግ እስከ መጠየቅ የደረሰ እርምጃ እንደሚወስድ በላይ ተሰማ ነግረውናል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ገዛ ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page