ተቋማት ተፈላጊ እንዲሆኑ ለማስቻል ተቋማትን የሚመዝንበትን ሞዴል እየከለሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ተናገረ፡፡
- 21 minutes ago
- 1 min read
የካቲት 11/2018
ተቋማት በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እና ተፈላጊ እንዲሆኑ ለማስቻል ተቋማትን የሚመዝንበትን ሞዴል እየከለሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ተናገረ፡፡
የሽልማት ድርጅቱ በሀገር ውስጥ ያሉ አምራች እና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በአለም አቀፍ የገበያ መድረክ ላይ ብቁ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አለም አቀፉ ገበያ የሚፈልጋቸው አዳዲስ መመዘኛ ሞዴሎችን አካትቻለሁ ብሏል፡፡
ከዚህ ቀደም ተቋማት ሲመዘኑ በመስፈርትነት ያልተካተቱ ፤ የአሰራር ሥርዓቶች እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በተመለከተ አዲስ በተከለሰው ሞዴል እንዲካተቱ መደረጉንም ሰምተናል፡፡
ለአብነት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመረዳት እና መጠቀምን እንደ አንድ መመዘኛ እንዲሆን መደረጉም ተነግሯል፡፡
ይህን የነገሩን የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ መብራት ናቸው፡፡

የሽልማት ድርጅቱ በአዲስ እየከለስኩት ነው ካለው የተቋማት መመዘኛ ሞዴሎች ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባሻገር የአምራቾችም ሆነ የአገልግሎት የአሰጣጥ እና የአሰራር ሥርዓት ይገኝበታል፡፡
ቡና ላኪዎችን በተመለከተ የአውሮፓ ህብረት ያወጣው መስፈርት እንደተካተተም ዋና ስራ አስፈፃሚው ያነሳሉ፡፡
ከዚህ ቀደም በሽልማት ድርጅቱ የልህቀት ዋንጫ የተሸለመው አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አሁን ላይ በአለም አቀፉ ገበያ ተወዳዳሪ መሆን እንደቻሉም ይናገራሉ፡፡
በኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት እየተከለሰ ያለው የተቋማት መመዘኛ ሞዴል ከቀናት በኋላ ተጠናቆ ይፋ እንደሚደረግም ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7








