የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን የኃይል አቅርቦት ሳይቆራረጥ እንዲያገኝ የሚያስችል የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ መስራቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- 2 hours ago
- 1 min read
ጥር 25/2018
የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን የኃይል አቅርቦት ሳይቆራረጥ እንዲያገኝ የሚያስችል የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ መስራቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ፡፡
የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከዚህ በፊት የራሱ ብቸኛ መስመር ስላልነበረው የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ያጋጥመው ነበር ተብሏል፡፡
አሁን ላይ ከአዳማ ቁጥር 3 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በቀጥታ አራት ባለ 33 ኪሎ ቮልት መካከለኛ መስመሮች ለፓርኩ መዘርጋቱን አገልግሎቱ አስረድቷል፡፡

ማከፋፋያ ጣቢያው 40 ሜጋ ዋት ኃይል ለፓርኩ በቀጥታ ማቅረብ የሚያስችል ዓቅም ያለው ሲሆን፤ አምራች ኢንዱስትሪዎቹ አሁን የሚጠቀሙትን የኃይል መጠን ያሳድገዋልም ተብሏል፡፡
አሁን ላይ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እያደገ እና ኢንዱስትሪዎች እየሰፉ መሄዳቸውን ተከትሎ ዘላቂ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እነዚህን ፍላጎቶች በፍጥነት፣ በፈጠራ እና በቅልጥፍና ለማሟላት እየሰራ እንደሚገኝ በላከልን መግለጫ ላይ ጠቅሷል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7












Comments