top of page

በአገራዊ ምክክሩ እየተሳተፉ ያሉ ቤተ እስራኤላውያን ከምክከሩ በኋላ እውቅና ይሰጠናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናገሩ፡፡

  • 2 hours ago
  • 1 min read

ነሐሴ 1 2018


በአገራዊ ምክክሩ እየተሳተፉ ያሉ ቤተ እስራኤላውያን ከምክከሩ በኋላ እውቅና ይሰጠናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናገሩ፡፡

በኢትዮጵያ እስከሁን ድርሶብናል ላሉት "መገለል እና መገፋት "በዓይነትም፣ በገንዘብ ካሣ እንፈልጋለን ሲሉ በኢትዮጵያ የቤተ እስራኤል የልማት ድርጅት ፕሬዚዳንት አቶ በላይነህ ታዘብኩ ነግረውናል።


እየተካሄደ በሚገኘው የምክክር ሂደት ላይ እየተሳተፉ ያሉ 26 ቤተ እስራኤላውያን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የነበራቸው ድርሻ በአግባባቡ እንዲሰነድላቸው እና ማንነታቸውም እንዲታወቅላቸው መጠየቃቸውን አስረድተዋል፡፡


የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላውያን የማንነት እውቅና እና የሃይማኖት መሰል ጥያቄዎቻችን በምክከሩ ይፈታል የሚል ተስፋ አለን ብለዋል አቶ በላይነህ፡፡


ቤተ እስራኤላዊያን ህጋዊ እውቅና ያለው የአምልኮ እና የቀብር ስፍራ እንደሌላቸው የጠቀሱት ፕሬዚዳንት አቶ በላይነህ ታዘብኩ በዚህ ምክንያት የወከሉት መቸገራቸውን ዘርዝረዋል፡፡


ቤተ አስራኤላዊን በእጅ ሙያቸው፣ በሃይማኖታቸው እና በሌላው ማህበራዊ ህወይታቸው ተገለዋል ያሉት አቶ በላይነህ "ቡዳ" ፣"ካይላ"፣" ፉጋ" እና "ቂሌ" እየተባሉ ሰም እየጠሰጣቸው ሲገለሉ ኖረዋል ብለዋል አቶ በላይነህ፡፡


ክምክክሩ በኋላ የማንነት አውቅና ይሰጠናል፣ ህጋዊ የሆነ የአምልኮ እና የቅብር ስፍራም እናገኛለን የሚል ተስፋ አለን ሲሉ የቤት እስራኤል የልማት ድርጅት ፕሬዚዳንት አቶ በላይነህ ታዘብኩ ተናግረዋል፡፡


አሁን ላይ በሁሉም ክልሎች ቤተ እስራኤላዊን አሉብን እናስባለን ያሉት ፕሬዚዳንቱ በማንነታቸው ላይ በሚደርሰው መገለል ግን እራሳቸውን ደብቀው ነው የሚኖሩት ብለዋል፡፡


በዚህም ምክንያት በአሁኑ ወቅት ምን ያክል ቁጥር ያላቸው ቤተ እስራኤላዊን በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ማወቅ አልቻልንም ሲሉ አክለዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....



ያሬድ እንዳሻው

Recent Posts

See All
በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ወሰነ።

ነሐሴ 2018 በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ወሰነ። የተላለፈው መግለጫ ከዩቲዩብ እንዲወርድ እና ይቅርታ እንዲጠየቅ ፍርድ ቤቱ አዟል። ዐቃቤ ሕግ አርቲስቶቹ በፍርድ ቤት

 
 
 
በቅርቡ የፀደቀውን ‘‘የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ‘‘ መመሪያን ባለመተግበር ሳይበር ጥቃት በተቋሙ ላይ የአገልግሎት መቋረጥን፣ የሀገር ደህንነት ማናጋት እና በዜጎች ህይወት ላይ ጉዳት ካደረሰ ሀላፊዎች ወይንም ሰራተኞች ከ7 አመት እስከ 10 አመት ፅኑ እስራት እንደሚቀጡ በአዋጁ መደንገጉ ተነገረ።

ነሐሴ 1 2018 በቅርቡ የፀደቀውን ‘‘የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ‘‘ መመሪያን ባለመተግበር ሳይበር ጥቃት በተቋሙ ላይ የአገልግሎት መቋረጥን፣ የሀገር ደህንነት ማናጋት እና በዜጎች ህይወት ላይ ጉዳት ካደረሰ ሀላፊዎች ወይንም ሰራተኞች ከ7 አመት እስከ 10 አመት ፅኑ እስራት እንደሚቀጡ በአዋጁ

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page