top of page

የመንግስት መ/ቤቶች ከህግ ውጪ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ አውጥተው ግዢ ፈፅመዋል፡፡

  • 3 hours ago
  • 1 min read

የመንግስት መ/ቤቶች ከህግ ውጪ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ አውጥተው ግዢ ፈፅመዋል፡፡


በ2017 በጀት ዓመት 72 የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከግዢ ህግ ውጪ የ1.2 ቢሊዮን ብር ግዢ መፈፀማቸው በኦዲት ተረጋገጠ፡፡


የገንዘብ መጠኑ ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲመሳከር የ800 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አለው፡፡


የፌዴራል መንግሥት ባወጣው የግዥ አዋጅ መሰረት ምን ያክል መስሪያ ቤቶች በጨረታ መግዛት ለሚገባቸው ግዥዎች ጨረታ አውጥተዋል እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሰብሰበዋል የሚለውን ለማረጋገጥ በተሰራ ኦዲት 72 መስሪያ ቤቶች ከህግ ውጭ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ግዢ መፈጸማቸውን ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አረጋግጧል፡፡



በዚህም በ29 መሥሪያ ቤቶች በጨረታ መፈጸም ሲገባቸው ያለ ጨረታ በቀጥታ የ441,033,011 ብር ግዢ መፈጸማቸው ተረጋግጧል፡፡


አንድ መሥሪያ ቤት ደግሞ በግልጽ ጨረታ መፈጸም ሲገባው መስፈርቱን ሳያሟላ በውስን ጨረታ የ134,295,220 ብር ጨረታ መፈፀሙን ዋና ኦዲተር ተናግሯል፡፡


እንዲሁም በ22 መሥሪያ ቤቶች ጨረታ ሳይወጣ በዋጋ ማወዳደሪያ 68,534,060 ግዢ የተፈጸመ ሲሆን በ17 መስሪያ ቤቶች ደግሞ በዋጋ ማወዳደሪያ ግዢ መፈጸም ሲገባቸው 409,691,138 ግዢ ፈፅመዋል፡፡


በተጨማሪም 3 መሥሪያ ቤቶች ያለ መስፈርት የ11,170,882 ብር ለቀማ ግዢ ፈጽመዋል፡፡


በተጨማሪም 20 መስሪያ ቤቶች ያለ ኤሌክትሮኒክስ የ194,793,839 ብር ግዢ ፈፅመዋል ይላል ዋና ኦዲተር፡፡


በዚህም በጠቅላላው በብር ከ1 ቢሊዮን 259 ሚሊዮን ብር በላይ ከህግ ውጭ ግዢ የተፈፀመ ሲሆን ይህም ከ2016 ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ800 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አለው፡፡


በ2016 በጀት ዓመት ተቋማት ከህግ ውጪ የፈፀሙት የግዢ መጠን 404 ሚሊዮን ነበር፡፡


ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት እነዚህ ተቀሟት ከህግ ውጭ ግዢ እንደፈፀሙ ማሳሰቡን በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡

 

ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…








1 Comment


kiki
kiki
2 hours ago

very informative and inpresssive, great. --recordly

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page