top of page

በስጦታና በተለያየ መንገድ ከሃገር ወጥተው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ቅርሶች ለህዝብ እይታ ክፍት ሊሆኑ ነው፡፡

  • 3 hours ago
  • 1 min read

ሰኔ 12/2018


በስጦታና በተለያየ መንገድ ከሃገር ወጥተው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ቅርሶች ለህዝብ እይታ ክፍት ሊሆኑ ነው፡፡


ከመጭው ዓመት ጀምሮ በመቅደላ ጦርነት ወቅት ተዘርፈው ተወስደው የነበሩና ከእንግሊዝ የተመለሱ ቅርሶችን ጨምሮ ሌሎችንም ለጉብኝት ክፍት ለማድረግ እየሰራሁ ነው ያለው የኢትዮጵያ የቅርስ ባለስልጣን ነው፡፡


ቅርሶቹ ለህዝብ እይታ ክፍት የሚሆኑት በአዲስ አበባ ብሔራዊ ሙዚየም ውስጥ እንደሆነም ሰምተናል።


ይሁን እንጂ ይህ ቋሚ ማሳያ ማዕከል ለተመለሱት ቅርሶች በቂ ባለመሆኑ ሁሉንም ማሳየት እንደማይቻልም ባለስልጣኑ ተናግሯል።


በሌላ በኩል በዚህ ዓመት ብቻ 21 ቅርሶች ከተለያዩ የአለም ሀገራት መመለሳቸውንም ሰምተናል።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አበባው አያሌው ባለፉት አምስት ዓመታት ከተለያዩ የአለም ሀገራት በዘረፋ፣ በስጦታና በተለያዩ መንገዶች ከሀገር የወጡ ቅርሶችን በማስመለስ በኩል ሰፊ ስራ ተሰርቷል ብለዋል ።


በዚህ ዓመትም ወደ 21 ገደማ ቅርሶችን ማስመለስ ተችሏል ሲሉ አስረድተዋል ።


በዚህ አመት ከተመለሱት ቅርሶች መካከል በመቅደላ ጦርነት ወቅት በእንግሊዝ የተወሰዱ ቅርሶች ይገኙበታል ።


ባለፉት አምስት እና ስድስት ዓመታት ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የነበሩ ከ 100 በላይ ቅርሶችን አስመልሰናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ እነዚህን ቅርሶች የውጭ ቱሪስቶችን እንዲስቡ፣ህብረተሰቡም ታሪኩን እንዲያውቅና እንዲመለከት ቅርሶቹን በአንድ ማዕከል በማደራጀት ለህዝብ ይፋ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።


በተለያዩ መንገዶች ከኢትዮጵያ ወደ ሌሎች የዓለም ሀገራት የወጡ ቅርሶችን ለማስመለስ የዲያስፖራው ማህበረሰብ ሚና ከፍተኛ መሆኑንም አቶ አበባው ነግረውናል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ...





ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…









Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page