top of page

ከመንግስት መ/ቤቶች የጠፉ እና የባለቤትነት መታወቂያ ደብተራቸው በሌሎች ድርጅቶች ተመዝግቦ የተገኙ ተሽከርካሪዎች መኖራቸው በኦዲት ተረጋገጠ፡፡

  • 7 hours ago
  • 1 min read

ሰኔ 12/2018


ከመንግስት መ/ቤቶች የጠፉ እና የባለቤትነት መታወቂያ ደብተራቸው በሌሎች ድርጅቶች ተመዝግቦ የተገኙ ተሽከርካሪዎች መኖራቸው በኦዲት ተረጋገጠ፡፡


የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የመስሪያ ቤቶችን የተሽከርካሪ አያያዝና ስምሪትን በተመለከተ ባካሄደው ምርመራ በተለያዩ መ/ቤቶች ዘጠኝ መኪኖች ከናካቴው ጠፍተዋል ብሏል፡፡


ተጨማሪ ስድስት ሞተር ብስክሌቶችም የጠፋባቸው መ/ቤቶችን አግኝቻለሁ ብሏል፡፡


የተቋማቱን ስም ግን በኦዲት ሪፖርቱ አልተጠቀሰም፡፡

በሌላ በኩል የባለቤትነት መታወቂያ ደብተራቸው በሌሎች መ/ቤቶችና ድርጅቶች ስም ተመዝግቦ የተገኘ 595 የመንግስት ተሽከርካሪዎች በኦዲት ምርመራው ተገኝተዋል፡፡


እንዲሁም የሰሌዳ ቁጥር የሌላቸው 13 መኪኖች፣ 10 የሞተር ብስክሌቶችና 20 ትራክተሮች የንብረት አያያዛቸው በተፈተሹባቸው የመንግስት ተቋማት መገኘታቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በሪፖርቱ ተናግሯል፡፡


ሌሎች 146 መኪኖች ፣ 27 ሞተር ብስክሌቶች፣ 18 የቁፋሮ መኪኖች ፣ 1 ሎደርና 1 ትራንክተር የሊብሬ ወይም የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር ሊቀርብላቸው አልቻለም ተብሏል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…









Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page