top of page

በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ ወደ ቀድሞ ቄያቸው ምስራቅ ወለጋ ጉብሰዮ ወረዳ የተመለሱ ከ141 በላይ አባዎራዎች ድጋፍ ስለተቋረጠባቸው መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡

  • sheger1021fm
  • 1 hour ago
  • 1 min read

ታህሳስ 6 2018


በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ ወደ ቀድሞ ቄያቸው ምስራቅ ወለጋ ጉብሰዮ ወረዳ የተመለሱ ከ141 በላይ አባዎራዎች ድጋፍ ስለተቋረጠባቸው መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡


የአካባቢው ቡሣ ጎኖፋ ወይም የእርዳታ ማስተባበሪያ በበኩሉ ድጋፍ እንዲቀጥል ለሚመለከተው የበላይ አካል ባሳውቅም ድጋፍ ግን ሊቀጥል አልቻለም ብሏል፡፡


በምስራቅ ወለጋ ጉቡሰዮ ያሉ ተፈናቂዎች የካቲት 11 ቀን 20015 ዓ.ም በአካባቢው አንፃራዊ ሰላም በመፈጠሩ ተጠልለው ከሚገኙበት የደብረብርሃን መጠለያ ጣቢያ ወደ ቀድሞ ቀያቸው የተመለሱ ናቸው፡፡


አሁን ላይ ወቅቱን ያለጠበቀ ድጋፍ ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች ከሚቀርብላቸው ውጪ እንደቀድሞ ምንም አይነት ድጋፍ እንደማይቀርብላቸውም ተናግረዋል፡፡


ለወረዳው ቡሳ ጉኖፋ ብናሳውቅም ምንም አይነት መፍትሄ ማግኘት አልቻልንም የሚሉ ተፈናቃዮቹ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ወደ ደብረ ብርሃን እንደተመለሱ አና በራሳችን እንኳን የቀን ስራ ሰርቶ ለማደር ተቸግረናል ይላሉ፡፡


ድጋፉ ለምን ተቋረጠ ያልነው የወረዳው ቡሣ ጎኖፋ በቅርቡ አንድ ግብረ ስናይ ድርጅት ያመጣው እርዳታ ድርጅቱ ይሰጥልኝ ባለው መሰረት ማከፋፈሉንና ከመንግስት በኩል ይቀርብ የነበረው ድጋፍ መቋረጡን ተናግሯል፡፡


ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ በአካባቢው ሰላም በመኖሩ ተፈናቃዮች ወደ ቤት ንብረታቸው ተመልሰው እንደቀደሞ አቸው እንዲኖሩ ተብሎ ነው ብሏል፡፡


ተፈናቃዮቹ አሁን በኪራይ ቤት እየኖሩ እንደሆነ እና ወደ ቤት ንብረታችን መልሱን ብንልም የሚሰማን አጥተናል ጠብቁ ነው የምንባለው ሲሉ ነግረውናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page