top of page

የህፃናት ካንሰር ህክምና ለማግኘት በአማካይ እስከ 6 ሰዓት መጓዝን እንደሚጠይቅ ተነገረ።

  • sheger1021fm
  • 49 minutes ago
  • 1 min read

ጥር  21/2018

 

የህፃናት ካንሰር አሳሳቢነት በየጊዜው እየጨመረ ቢመጣም፣ በአግልግሎት አለመስፋፋት ምክንያት  ህክምናውን ለማግኘት በአማካይ እስከ 6 ሰዓት መጓዝን እንደሚጠይቅ ተነገረ።

 

በኢትዮጵያ የህፃናት ደምና ካንሰር ህክምና ማህበር በዓመት በካንሰር ከሚጠቁ አጠቃላይ ሰዎች 10 በመቶዎቹ ህፃናት ቢሆንም ህክምና የሚያገኙት ግን 25 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው ብሏል።

 

ከህክምናው አለመስፋፋት በተጨማሪ፣ ህክምናው የሚጠይቀው የገንዘብ አቅምና የህብረተሰብ የጤና መድህን አለመስፋፋት ፈተና እንደሆነ መቀጠሉን የማህበሩ ዋና ፕሬዝዳንት ዶ/ር አቤል ኃይሉ ነግረውናል።

 

በህክምና ወቅት ህፃናት ደም በማጣት ይሞታሉ ያሉት ዶ/ር አቤል፣ አሁን ያለውን የደም ዕጥረት ለማስቀረት ከአጠቃላዩ የህዝብ ቁጥር  61 በመቶው  ደም መለገስ ይኖርበታል ብለውናል።

 

ያሉን የህፃናት ካንሰር ሃኪሞች ከ20 አይበልጡም ያሉት ኃላፊው በየአመቱ ከሚጨምረው የታማሚዎች  ቁጥር አንፃር ብዙ መሰራት እንዳለበት አንስተዋል።

 

ዶ/ር አቤል የህፃናት ካንሰር ህክምናን የሚሰጡ የጤና ማዕከላትም በቁጥር 8 ብቻ መሆናቸውን ነግረውናል።

 

ብዙ ወላጆች ካንሰር አይድንም የሚል የተሳሳተ አመለካከት እንዳለባቸው የነገሩን ዶ/ር አቤል ነገር ግን የህፃናት ካንሰር ሳይዘገይ ተገቢውን ህክምና ካገኘ 85 በመቶ የመዳን ዕድል አለው ብለውናል።

 

እንደ የካንሰር ህመሙ አይነት ቢለያይም መቶ በመቶ የመዳን ዕድል ያለው የህፃናት ካንሰር እንዳለም ነግረውናል።

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

ንጋት መኮንን

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page