top of page

አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ-ጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

  • 2 hours ago
  • 1 min read

መጋቢት 29/2018


አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ-ጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።


አምባሳደር ቆንጂት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከ1950ዎቹ አንስቶ ከዴስክ ኦፊሰርነት እስከ ከፍተኛ ሀላፊነት ማገልገላቸው ተነግሯል።


አምባሳደር ቆንጂት የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ከመመስረቱ አንድ ዓመት አስቀድመው ወደ ዲፕሎማትነት ህይወት መግባታቸው ይነገራል።



በዲፕሎማትነት ሀገራቸውን በማገልገል ቀዳሚ ከሆኑ ሴት አፍሪካዊ ዲፕሎማቶች ውስጥ አንዷ ተደርገውም ስማቸው ይነሳል።


ለዚሁ የረጅም ጊዜ አገልግሎታቸውን ከዚህ ቀደም በሀገር ደረጃ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።


#አምባሳደር_ቆንጂት ከዮዲት እምሩ በመቀጠል፤ በኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሴት አምባሳደርም ናቸው።


አምባሳደሯ በኦቶዋ፣ ካይሮ፣ ቴል አቪቭና ቬይና በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፤ በአፍሪካ ሕብረትና በተባባሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ መልዕክተኛ በመሆንም ማገልገላቸውን ታሪካቸው ይናገራል።


ከሰኔ 2009 እስከ መስከረም 2011 ዓ.ም ደግሞ ኢጋድ በመራው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ላይ ልዩ አማካሪ ሆነው ማገልገላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።


አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ-ጊዮርጊስ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተነግሯል።

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page