የ1997 እና የ2005 ዓ.ም የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን የሚቆጥቡ የማህበረሰብ ክፍሎች
- sheger1021fm
- 21 minutes ago
- 1 min read
ታህሳስ 16/2018
የጋራ መኖሪያ ቤት ለማግኘት ተመዝግበው የሚጠባበቁ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ፡፡
እጣ ፈንታችን ምንድነው? ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በበኩሉ በተለያየ መልኩ እየተተገበሩ ባሉ ፕሮግራሞች ቤት የማግኘት እድል አላቸው ብሏል፡፡
እነዚህ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን የሚቆጥቡ የማህበረሰብ ክፍሎች የ1997 እና የ2005 ዓ.ም መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ከዚህ ቀደም የሚመለከታቸው የሚባሉ የስራ ሀላፊዎችን መጠየቃቸውና መፍትሄ ማግኘት እንዳልቻሉም ያስረዳሉ፡፡
ነዋሪዎቹ ቁጠባቸውን እንዳላቋረጡ እና አሁን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር እያስገነባ ከሚገኘው ቤት የማግኘት እድል ይኖረናል ወይ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዲሳ አራርሶ የ1997 እና የ2005 ዓ.ም የቤት ቆጣቢዎችን በአስራ አራተኛው ዙር የመጨረሻው ዕጣ ሲወጣ እንደ የቤት ፍላጎታቸው ሙሉ የቆጠቡትን አዳርሰናል ማለት ይቻላል ሲሉ መልሰዋል፡፡
ሆኖም ቀረን የሚሉ ካሉ አሁንም ቤት የማግኘት እድል አላቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1








