የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን ሙሉ ለሙሉ ለመስጠት የግብዓት እጥረት እንደገጠማቸው ያነጋገርናቸው ክልሎች ተናገሩ፡፡
- 12 minutes ago
- 1 min read
ግንቦት 20/2018
የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን ሙሉ ለሙሉ ለመስጠት የግብዓት እጥረት እንደገጠማቸው ያነጋገርናቸው ክልሎች ተናገሩ፡፡
ከሰኔ 24 ጀምሮ የሚሰጠው የ12ተኛ ክፍል ፈተና ሙሉ ለሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ትምህርት ሚኒስቴር ዝግጅት ማጠናቀቁን በተለያዩ ጊዜያት መነገሩ ይታወሳል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ፤ በክልሉ ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል በኦንላይን መፈተን የሚችለው 76 በመቶ ብቻ መሆኑን አስረድቷል፡፡
በቀሪ ጊዜ ይህንን ቁጥር ወደ 80 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን ቢሮው የጠቀሰ ሲሆን ዘንድሮ 24 በመቶ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞችን በወረቀት ለመፈተን እየተዘጋጀ መሆኑን ነግሮናል፡፡
ለፈተናው የሚያስፈልጉ የኮምፒዩተር እጥረት፣ የኢንተርኔት አለመሟላት እና ሌሎች ግብአቶች እጥረት ማጋጠሙ ተሰምቷል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ በበኩሉ ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል 65 ከመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ብቻ በኦንላይን ይፈተናሉ ብሏል፡፡
ቀሪውዎቹ በወረቀት እንደሚፈተኑ የተነገረ ሲሆን በኦንላይን የሚፈተኑ ተማሪዎች ሰሞኑን የሙከራ ፈተና እየወሰዱ ነው ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ.......
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments