ዘንድሮ በሚካሄደው ሰባተኛ ሀገራዊ ምርጫ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የተሻለ ድምፅ በፓርላማው እንዲኖራቸው እንደሚፈልጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
- sheger1021fm
- 7 minutes ago
- 1 min read
ጥር 26/2018
ዘንድሮ በሚካሄደው ሰባተኛ ሀገራዊ ምርጫ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የተሻለ ድምፅ በፓርላማው እንዲኖራቸው እንደሚፈልጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
መንግስት ስራውን ትቶ በምርጫ ስራ ላይ አተኩሯል በሚል ለቀረበው ጥያቄ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲመልሱ ብልፅግና ፓርቲ ምርጫው ላይ አተኩራችሁ እየሰራችሁ አይደለም ዋና ትኩረታችን በመንግስት ስራ ላይ ነው እያሉን ነው ብለዋል።
ከምርጫ ቅስቀሳ ጋር በተያያዘ ወጣቱን ለመድረስ አሁን ያሉ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም የተሻለ ነው የህዝብ መገናኛ ብዙሃን ለሁሉም እኩል ተደራሽ እንዲሆን እንሰራለን ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ።
ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ለምርጫው ስጋት ነው ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ ሲመልሱ ባለፉት 6 ወራት በተደረጉ የአደባባይ በዓላት ምንም ችግር ሳይፈጠር ተጠናቋል ታዲያ ምርጫው ሲደረግ እንዴት የፀጥታ ስጋት ይሆናል ሲሉም ጠይቀዋል።

መንግስት ምርጫውን ለማድረግ ዝግጁ ነው በምርጫው የተፎካካሪ ፓርቲዎች የድምፅ ተሳትፎ ከባለፈው የተሻለ እንዲሆን ነው እየሰራን ያለነው ብለዋል።
በሀገራዊ ምክክር ማንም እንዲሳተፍ ነው የተፈቀደው ፍላጎት የሌለውን ቡድን ግን ማስገደድ አይቻልም ሲሉም ተናግረዋል።
የኮሚሽኑ ቀጣይ ስራ ተወያዮችን አወያይቶ ለመንግስትና ለምክርቤቱ ምክረ ሀሳብ ማቅረብ ነው ተብሏል።
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7








