በተለይ የወልቃይት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ያልሆነው ተፈናቃይን መያዣ ያደረገ ፖለቲካ በመኖሩ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተናገሩ፡፡
- sheger1021fm
- 2 hours ago
- 1 min read
ጥር 26/2018
በተለይ የወልቃይት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ያልሆነው ተፈናቃይን መያዣ ያደረገ ፖለቲካ በመኖሩ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተናገሩ፡፡
በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ተፈናቅለው ወደ ትግራይ ሂደው የነበሩ የኤሊባቡር እና ራያ አካባቢ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመልሰው በሰላም እየኖሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ይሁንና የወልቃይት ተፈናቃዮችን የመመለሱ ነገር አስቸጋሪ ሁኔታ እንደገጠመው ተናግረዋል፡፡

በወልቃይት ጉዳይ በትግራይና አማራ ክልል መካከል ለረዥም ጊዜ የይገባኛል ጥያቄ መኖሩን ለዚህም የፌዴራል መንግስቱ ተፈናቃዮች ተመልሰው በሪፈንደንም ራሱ ነዋሪው ውሳኔ እንዲሰጥ አቋም መያዙን አንስተዋል፡፡
ተፈናቃዮቹም ለመመለስ፣ የተፈናቀሉበት አካባቢም ለመቀበል ዝግጁ ቢሆኑም ተፈናቃይን እንደመያዣ የሚጠቀም ፣ ስቃይ ዘርቶ እገዛ ከሌሎች የሚጠብቅ ፖለቲካ በመኖሩ ተፈናቃዮቹን ለመመለስ አስቸጋሪ ስለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ ጠቅሰዋል፡፡
የወልቃይትን ጉዳይ ፓርላማውም እኔም መወሰን አንችልም ፤ መወሰን የሚችለው የአካባቢው ነዋሪ የሆነው ህዝብ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርቲዎች ለዚህ አስቻይ ሁኔታ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ከሰሜኑ ጦርነት ውጭ የተፈናቀሉ እና እስካሁን ወደ ቀያቸው ያልተመለሱ ሰዎችን ጉዳይ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው አላነሱም፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7












Comments