top of page

መሬት በኢትዮጵያ ትልቅ የገቢ ምንጭ እና  የፖለቲካ ስርዓቱም ዋነኛ ትኩረት ቢሆንም እስከዛሬም ያልተፈታ አስተዳደራዊ ችግር እንዳለበት ይነገራል፡፡

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 1 min read

ጥር 26/2018

 

መሬት በኢትዮጵያ ትልቅ የገቢ ምንጭ እና  የፖለቲካ ስርዓቱም ዋነኛ ትኩረት ቢሆንም እስከዛሬም ያልተፈታ አስተዳደራዊ ችግር እንዳለበት ይነገራል፡፡

 

ይህም ሃገር ማግኘት ያለባትን ሃብት እንዳታገኝ ከማድረጉም በላይ ለሙስናና የዕርስ በዕርስ ግጭት መነሻ መሆኑን ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

 

በሃዋሳ ዩንቨርሲቲ የመሬት የህግ ጉዳዮች ተመራማሪ የሆኑት ዳንኤል በኃይሉ (ዶ/ር) መሬትን የሚያህል ሃብት በሚኒስቴር መስሪቤት የሌለው መሆኑ አንዱ የአስተዳደር ስርዓት ክፍተት ነው ይላሉ፡፡

 

ባለሙያው ኢትዮጵያ የመሬት አስተዳደር ስርዓቱን ባለማስተካከሏ ብቻ በብዙ ቢሊየን ገንዘብ እንዳጣች ያነሳሉ፡፡

 

ለዚህም ባለሙያው የሩዋንዳን ተሞክሮ የጠቀሱ ሲሆን ከኢትዮጵያ  ከ30 በመቶ በታች የመሬት ይዞታ ያላት ሩዋንዳ የአስተዳደር ስርዓቷን በማስተካከል ብቻ በ 10 በቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደምታገኝ ይጠቅሳሉ፡፡

 

በኢትዮጵያ ጠንካራ የመሬት አስተዳደር መዋቅር አለመኖሩ መሬት ተጠቃሚ ነኝ የሚለው ሁሉ እየተነሳ የሚያዝበትን ስርዓት ፈጥሯል የሚሉት ባለሙያው ይህም ስርዓት የለሽነትን አምጥቷል ይላሉ፡፡

 

አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ ከ 100 ሺህ በላይ የመሬት ይዞታ ባለሙያዎች ያስፈልጓታል የሚሉት ዳንኤል በኃይሉ (ዶ/ር) አሁን ያሉት ግን 30 በመቶ እንኳን አይደርሱም፡፡

 

ያሉት ሰራተኞችም በፖለቲካ ሹመት የተመደቡ እንጂ በመሬት ይዞታ ላይ በቂ ዕውቀት የሌላቸው እነደሆኑ ባለሙያው ይጠቅሳሉ፡፡

 

ይህም “ለሀገር የመሬት ሃብት በረከት መሆን ሲገባው እርግማን ሆኖባታል” ይላሉ፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

 

ንጋት መኮንን

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

 

 

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page