top of page

ዘመን ባንክ አጠቃላይ ሀብቴ ከ100 ቢሊዮን ብር አለፈ አለ፡፡

  • sheger1021fm
  • 18 hours ago
  • 1 min read

ጥር 19/2018


ዘመን ባንክ አጠቃላይ ሀብቴ ከ100 ቢሊዮን ብር አለፈ አለ፡፡


የተከፈለ ካፒታሉም14 ቢሊዮን ብር መድረሱን በላከልን መግለጫ ላይ ጠቅሷል፡፡


ባንኩ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ አጠቃላይ ሀብት 106 ቢሊዮን ብር፣ ተቀማጭ ገንዘብ ደግሞ 80 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተናግሯል፡፡


ይህም ባንኩ የተረጋጋ ዕድገትና ጠንካራ የደንበኞች አመኔታ እንዳለው የሚያሳይ ነው ሲሉ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ዘበነ አስረድተዋል፡፡


ዘመን ባንክ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡም ተጠቅሷል፡፡


ዋና ስራ አስፈጻሚው የባንኩ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ ስኬት ካለፈው ዓመት ከነበረው የሥራ አፈፃፀም ጋር ሲወዳደር የዘንድሮው የላቀና ስኬታማ የሥራ ጊዜ ያሳለፍንበት ነበር ሲሉ አስረድተዋል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page