top of page

ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው የ500 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ ላይ  የ92 ሚሊዮን ዶላር ክፍተት(ተጨማሪ ፍላጎት) ተፈጠረ፡፡

  • sheger1021fm
  • 12 minutes ago
  • 1 min read

ጥር 19/2018


ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው የ500 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ ላይ  የ92 ሚሊዮን ዶላር ክፍተት(ተጨማሪ ፍላጎት) ተፈጠረ፡፡


ይህም ባንኩ ባቀረበው የውጪ ምንዛሬ መጠንና በተፈለገው መጠን መካከል ያለውን ክፍተት ይፋ ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡


ማዕከላዊ ባንኩ ዛሬ 500 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ ያቀረበ ሲሆን የተጫራች ባንኮች ፍላጎት ግን 592.3 ሚሊዮን ዶላር አንደሆነ የባንኩ መረጃ ያሳያል፡፡


የባንኩ ጨረታ ከባለፈው ጋር ሲነጻጸር የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም በ11 ሳንቲም ያጠናከረ ሆኗል፡፡


ጥር 12 ቀን 15 ዙር ጨረታውን አድርጎ የነበረው ብሔራዊ ባንክ 16 ዙር የውጭ ምንዛሬ ጨረታውን ዛሬ አካሂዷል፡፡

በዚህም መሰረት የቀረበው የ500 ሚሊዮን ዶላር ምንዛሬ በአማካኝ አንድ የአሜሪካን ዶላራ በአማካኝ 154.81 ብር ተሸጧል፡፡


የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ላይ 31 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን ከባለፈው ጨረታ አንጻር ሲተያያይ የ10 ባንኮች ብልጫ አለው፡፡


በዛሬው የውጭ ምንዛሬ ጭረታ ከ31 ባንኮች ውስጥ 25 ባንኮች አንድን ዶላር በ154.81 ብር በጨረታ ገዝተዋል ወይንም ዶላር አግኝተዋል፡፡


በባለፈው ጨረታ ግን የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የቻሉት በጨረታው ከተሳተፉ 21 ባንኮች ውስጥ 15 ብቻ ነበሩ ፡፡


ይህም ከዛሬው ጨረታ በ10 ባንኮች ያንሳል፡፡


ጥር 12 ቀን ቀርቦ ከነበረው የውጭ ምንዛሬ መጠን ዛሬ ለ16 ኛ ጊዜ የቀረበው በ430 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ እንዳለው ተነግሯል፡፡


በባለፈው ጨረታ ተፈጥሮ የነበረው ክፍተት የ24.7  ሚሊዮን ዶላር ነበረ።


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page