ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ለመጀመር እስካሁን ያደረገው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት እንዳላመጣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- Nov 17
- 2 min read
ህዳር 8 2018
ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ለመጀመር እስካሁን ያደረገው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት እንዳላመጣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡
ኮሚሽኑ ይህንን ያለው ካሳለፍነው ህዳር 5 እስከ 7 2018 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ከፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር በመከተበት ወቅት ነው፡፡
የተሳታፊ ልየታና የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራዎችን በማገባደድ ወደ ሃገራዊ ምክክር ጉዳኤው ለመሸጋገር የሚያስችሉትን ስራዎች እየከወነ መሆኑን የሚናገረው ኮሚሽኑ በሂደቱ የገጠሙትን ፈተናዎችም ጠቅሷል፡፡
ከችግሮቹ መካከል ቀዳሚው ነው ያለው እስካሁን ድረስ በትግራይ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ስራዎች አለመጀመራቸውን ነው፡፡

የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም ስለዚህ ሲያስረዱ ኮሚሽኑ ከፕሪቶሪያው ስምምነት መፈረም ማግስት ጀምሮ በትግራይ ክልል እንዴት ስራው ይሰራ በሚለው ጉዳይ ዙሪያ፤ ከህወሃት አመራሮችንና ከሌሎችም ባለድርሻዎች በተደጋጋሚ መነጋገር ችሏል ብለዋል፡፡
ይሁንና በውይይቶቹ ከህውሃት ወገን ከፕሪቶሪያው ስምምነት አተገባበር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ተነስተውልናል ያሉት ኮሚሽነር መላኩ ጥያቄዎቹ የፌድራል መንግስቱን የሚመለከቱ በመሆኑ ለመንግስት አቅርበን ምላሽም እንዲያገኙ ግፊት እያደረግን ነው፤ እስካሁን ችግሮቹ ባለመፈታታቸው በተያዘው እቅድ መሰረት ወደ ትግራይ ገብተን አጀንዳ ማሰባሰብ አልቻልንም ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ሌላውና ኮሚሽኑ በስራው ሂደት ገጠመኝ ያለው ችግር የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሟላ መልኩ አለመሳተፍ ነው፡፡

በሂደቱ በኢትዮጵያ ካሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች 80 በመቶዎቹ ከኮሚሽኑ ጋር እየሰሩ ቢሆንም ሂደቱን አቋርጠው የወጡ ፓርቲዎችን ለማካተት ፅህፈት ቤቱ ድረስ በመጥራት እያነጋገረ ነው ተብሏል፡፡
ፓርቲዎቹ ምክክሩን ለቅቀው ለመውጣቻቸው የሚያነሱት ምክንያት ፖለቲካዊ ነው፤ጥያቄያቸው ከመንግስት ጋር የተገናኘ ነው ብለዋል ኮሚሽነሩ፡፡
ኮሚሽኑ የገጠሙት ችግሮች ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው በመሆኑ ፖለቲካዊ ውሳኔ የሚፈልጉ ናቸው ያሉት ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ ናቸው፡፡
እስካሁን በምክክር ሂደቱ ያልተሳተፉ የታጠቁ ቡድኖችንና የፓለቲካ ፓርቲዎችን ለማሳተፍ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚቀጥል ያነሱት ዋና ኮሚሽነሩ በዚህ ዓመት ሃገራዊ ምክክሩንና ሃገራዊ ምርጫውን አጣጥሞ ማስኬድ ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡
የአጀንዳ ቀረፃ ስራውን በማጠናቀቅ ምክክር የሚደረግባቸውን አጀንዳዎች ይፋ ለማድረግ እየሰራ ነው መሆኑንም የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሲናገር ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments