ኮሜርሻል ኖሚኒስ ፊቱን ወደ የውጪ ሀገር የሰው ሀይል አቅርቦትም ፊቱን ማዞሩን ተናገረ፡፡
- 1 hour ago
- 1 min read
ግንቦት 28/2018
በሶስተኛ ወገን አገልግሎት ዘርፍ የጥበቃ፣ የፅዳት፣ የሀብትና ንብረት አስተዳደር ስራ 60 ዓመት የሞላው ኮሜርሻል ኖሚኒስ አሁን ደግሞ ፊቱን ወደ የውጪ ሀገር የሰው ሀይል አቅርቦትም ፊቱን ማዞሩን ተናገረ፡፡
በ1958 ዓ.ም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተቋቋመው ድርጅቱ ለመንግስታዊም ሆኑ ለግል ተቋማት የፅዳትና የጥበቃ አገልግሎት የሚሆኑ የሰው ሀይል ከማቅረብ በተጨማሪ ፣ ህንፃና ንብረት አስተዳደር ፣ ከካሳ ክፍያ ጋር የተያያዙ የፈንድ አስተዳደርን ጨምሮ 13 ዓይነት አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ተናግሯል፡፡
በዚህም በመላ ሀገሪቱ በሚገኙት 32 ቅርንጫፎቹ ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች የስራ እድል መፍጠሩን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ ነግረውናል፡፡
ድርጅቱ እስካሁን ሲሰጣቸው የነበሩ አገልግሎቶቹን ማዘመንና ማስፋት ላይ እንደሚበረታ እንዲሁም ወደ ውጪ ሀገር የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማቅረብ እየሰራ እንደሆነ አስረድቷል፡፡
ለዚህም አንዲያግዝ በአጠቃላይ 127 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የስልጠና ማዕከል በገርጂ አካባቢ ተከፍቶ ስራ ጀምሯል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7

