top of page

ከመንግስትጋር እርቅ አድርጎ ወደ ሰላማዊ ትግል የገባው አፋሕድ አጀንዳ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከበ።

  • sheger1021fm
  • 9 minutes ago
  • 2 min read

ጥር 28/2018

 

በኢትዮጵያ ገለልተኛ በሆነ ተቋም የህዝብ ቆጠራ እንዲካሄድ እና የአማራ ክልል ተወላጆችም በሚኖርበት ክልል የፖለቲካ ውክልና እንዲኖራቸው ከመንግስትጋር እርቅ አድርጎ ወደ ሰላማዊ ትግል የገባው አፋሕድ አጀንዳ አድርጎ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከበ።

 

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ ከድርጅቱ  አመራሮች እና ተወካይዎች ጋር ተወያይቶ  አጀንዳዎችን  ተረክቧል።

 

ደርጅቱ መሳሪያ አንስቶ ወደ ጨካ ለመግባት ምክንያት ሆነውኝ ነበር ያላቸውን በ17 ከፍል የተደራጁ አጀንዳዎቹን ለምክክር ኮሚሽን ዛሬ ከሰዓት በኋላ ማስረከቡን የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ ኢያሱ አባተ ነግረዉናል።

 

አቶ እያሱ የአማራ ክልል ህዝብ መፈናቀል ፣መሰደድ ፣ወሰን አለመከበር እና የማንንት ጥያቄዎች አለመመለስ ጫካ ለመግባት ምክንያት መሆናቸውን አስረድተዋል።

 

በትገራይና አማራ ክልል የይገባናል ጥያቄ የሚነሳባቸው የጠለምትና ራያ አካባቢዎችም ወደ አማራ ክልል እንዲካለሉ በአጀንዳነት ማስገባቱን ሰምተናል፡፡

 

በተጨማሪም  ህግ መንግስቱ  በተለይ እስከ መገንጠል የሚለው ከፍል ማሻሻያ  እንዲደረግበት አጀንዳ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

 

በአገሪቱ ተዓማኒ እና ገለልተኛ በመሆነ ተቋም የህዝብ ቆጠራ እንዲካሄድ አጀንዳ አድርጎ ያቀረበው ድርጅቱ የአማራ ተወላጅ የሆነ ኢትዮጵያ በማንነቱ ምክንያት በየትኛውም አካባቢ ችግር እንዳይደርስበት ፣እንዳይፈናቀል ፣በቋንቋው እንዲገለገል እና  በሚኖርበት ክልል የፓለቲካ  ውክልና እንዲኖረው በአጀንዳ መልክ መቅረቡን የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ ኢያሱ አባተ ነግረዉናል።

 

የእነዚህ አጀንዳዎች መመለስ ሰላማዊው የትግል መንገድ ለመረጥንው ለእኛ ብቻ ሳይሆን አሁን በጫካ የቀሩትም ይህን መንገድ እንዲከተሉ ይረዳል ሲሉም አቶ እያሱ አከለዋል።

 

የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ዐርዕያ  በበኩላቸው ስለ ኮሚሽኑ ዓላማ እና ተልዕኮ እንዲሁም  እስካሁን ተሰርተዋል ያሉትን ተግባራትን በተመለከተ በአጅዳ ርክክቡ ወቅት ዘርዝረዋል።

 

በአማራ ክልል በተደረገው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት 5545 ተሳታፊዎች ተሳትፈዋል ፤አጀንዳዎቻቸውንም አስረክበው የምጨርሻውን ጉባዔ እየተጠበቁ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

 

 

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ባሉ 11 ክልሎች አጀንዳ መሰብሰቡን ያስታወሱት ኮሚሽነር መሰፍን ከሀገር ውጪ በ6 አገራት ከሚገኙ እና ለመሳተፍ ፍቃደኛ ከሆነ ኢትዮጵያዊን አጀንዳዎችን ተረክበናል ሲሉ አስረድተዋል ።

 

ኮሚሽነሩ ከሁሉም ኢትዮጵያዊን የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን ኮሚሽኑ በቅርቡ ይፋ እንደሚደርግ ተናግረዋል ።

 

ዋና ዛሬ አጀንዳ ያስረከበውን አፍሃድ ጅርጅቱን አመስግነው ቀሪዎችም ይህን መንገድ እነወዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል ።

 

ያሬድ እንዳሻው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                    

 

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page