‘’ኢትዮጵያ ለህዳሴ ግድቡ ግንባታ፤ አንድም ብር እርዳታ፣ አንድም ብር ብድር አልወሰደችም’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ።
- Feb 3
- 1 min read
ጥር 26/2018
‘’ኢትዮጵያ ለህዳሴ ግድቡ ግንባታ፤ አንድም ብር እርዳታ፣ አንድም ብር ብድር አልወሰደችም’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ በፓርላማ ቀርበው እንደራሴዎች ባለፉት 6 ወራት የተከናወኑ የመንግስት ስራዎችን አሰመልክተው ላነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።

ግድቡን አንድ ብር እርዳታ ካለ አንድ ብር ብድር ያሳካ መንግስት እና ህዝብ ፕሮጀክት አይሰራም ማለት አይቻልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ።
በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ቁርጠኛ አቋም በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም ያሉ ጨክነው ስለሰሩ የተጠናቀቀ ፕሮጀክት ነው ብለዋል ዐቢይ።
357 የምክር ቤት አባላት በተገኙበት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10 መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ በማካሄድ ላይ ነው።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments