top of page

አዋሽ ኢንሹራንስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዦችን የጉዞ የጤና ኢንሹራንስ ሽፋን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ።

  • 3 hours ago
  • 1 min read

የካቲት 12/2018


አዋሽ ኢንሹራንስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዦችን የጉዞ የጤና ኢንሹራንስ ሽፋን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ።


ስምምነቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቺፍ ኮሜርሺያል ኦፊሰር አቶ ለማ ያዴቻ እና የአዋሽ ኢንሹራንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጅባት አለምነህ በዛሬው እለት ተፈራርመውታል።


በስምምነቱ መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዦች የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የሞባይል መተግበርያ ላይ የጉዞ ኢንሹራንስ ሽፋን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል።


የመድን አገልግሎቱ ተጓዦች ለተለያዩ ጉዳዮች ወደተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሲጓዙ ለሚያገጥማቸው የተለያዩ የጤና እክሎች እንደሚውል ተጠቅሷል።


የዋሽ ኢንሹራንስ ዋና ስራ አሰፈፃሚ አቶ ጅባት አለምነህ "ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከአለም አቀፍ የጠለፋ ኢንሹራንስ ዋስትና ሰጪ ተቋማት እና ትራቭል አሲስታንት ጋር በመሆን በጉዞ ወቅት የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ጉዳት የሚያካክስና የሚያቃልል አስተማማኝ የኢንሹራንስ ሽፋን አገልግሎትን በማቅረባችን ከፍተኛ የሆነ ደስታ ይሰማናል"ብለዋል።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቺፍ ኮሜርሺያል ኦፊሰር አቶ ለማ ያዴቻ በበኩላቸው "ምንም እንኳን ስምምነቱ የተደረሰው አዋሽ ኢንሹራንስ በጨረታ ተወዳድሮ አሸንፎ ቢሆንም ኩባንያው ከቢሮክራሲ የነፃ በቢዝነስ መርህ የሚሰራ ተቋም በመሆኑ አብረን በመስራታችን ደስተኞች ነን " ብለዋል።


አዋሽ ኢንሹራንስ ሰየተፈረመ ካፒታሉ 4 ቢሊዮን ብር፣ የተከፈለ ካፒታሉ ከ3.5 ቢሊዮን ብር፣ የኩባንያው አጠቃላይ ኃብት ደግሞ ከ 13 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል ተብሏል፡፡

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page