አንዳንድ የጸጥታ ችግር ባሉባቸው አካባቢዎችና የጤና አገልግሎት መስጫ ባልተስፋፋቸው ቦታዎች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት በሚፈለገው ልክ እየተተገበረ አይደለም ተባለ፡፡
- 10 minutes ago
- 1 min read
የካቲት 10/2018
አንዳንድ የጸጥታ ችግር ባሉባቸው አካባቢዎችና የጤና አገልግሎት መስጫ ባልተስፋፋቸው ቦታዎች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት በሚፈለገው ልክ እየተተገበረ አይደለም ተባለ፡፡
ከጸጥታ ስጋቱ በተጨማሪ ስለአገልግሎቱ የሚሰጡ የተሳሳቱ አስተያየቶችም ችግር መሆኑ ተነግሯል፡፡
የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት መጠቀም ቢፈልጉም በተለያየ ምክንያት ዕክል የገጠማቸው አፍላ ወጣቶች ላይ በማተኮር አገልግሎቱ እንዲስፋፋ እያደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
በቅርቡ በተከወነ ጥናት በሀገሪቱ የውልደት ምጣኔው መቀነሱ የተነገረ ቢሆንም አሁንም ግን የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎቱን ማስፋፋት ላይ የሚቀሩ ስራዎች አሉ የሚሉት በጤና ሚኒስቴር የስነ ተዋልዶ ጤና የቤተሰብ ዕቅድና የወጣቶች ፕሮግራም ሀላፊ የሆኑት ዶክተር አለማየሁ ሁንዱማ ናቸው፡፡

በተጨማሪም አንዳንድ የጸጥታ ችግር ባሉባቸው አካባቢዎችን ላይ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎቱ መስተጓጎል ገጥሞታል የሚሉት ዶክተር አለማየሁ በእነዚህ ቦታዎችም ላይ አገልግሎቱ እንዲሰጥ እና ወደ ቀድሞ እንዲመለስ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን በተለያዩ መንገዶች ተደራሽ ለማድረግ የሚከወኑ ስራዎች ቢኖሩም በማህበረሰብ ዘንድ ያለው ግንዛቤ ግን አሁንም ዝቅተኛ መሆኑ አገልግሎቱ በተፈለገው ልክ እንዳይሆን አድርጎታል ተብሏል፡፡
ትልቁ ነገር አንደኛው የአመለካከት ችግር ነው የሚሉት ኃላፊው የአመለካከት ወይም የግንዛቤ ችግር መኖሩን ሁለተኛው ደግሞ በተለይ ከሃይማኖት አባቶች እና ከተለያዩ አካላት ጋር የሚከወኑ ስራዎች መኖራቸው ተነግሯል፡፡
በሌላ በኩል ከአቅርቦት አንፃር የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት አገልግሎቱ ባልደረሰባቸው ቦታዎች ላይ መስራት ይገባል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ከተጀመረ ከ60 ዓመታት በላይ ቢያስቆጥርም አሁንም ግን የተጠቃሚዎቹ ቁጥር ካለው የህዝብ ቁጥር አኳያ ዝቅተኛ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ምህረት ስዩም
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7








