በአማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች በቀጠለ የሰላም እጦት ምክንያት የትምህርት ሥርዓቱ ጫና ውስጥ ወድቋል፡፡
- 35 minutes ago
- 1 min read
የካቲት 9/2018
በሰሜኑ ጦርነት እና አሁንም በአማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች በቀጠለ የሰላም እጦት ምክንያት የትምህርት ሥርዓቱ ጫና ውስጥ ወድቋል፡፡
ባለፉት አራት እና አምስት አመታት በክልሉ በነበሩ፣ አሁንም ድረስ በቀጠሉ ሰላም እጦቶች እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ባሉ ችግሮች ምክንያት ዘርፉ በብዙ ውጣ ውረድ እያለፈ ነው ያለው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለዚህም ድጋፍ እሻለሁ ብሏል፡፡
በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከ4 ሺህ ትምህርት ቤቶች በላይ ጉዳት የደረሰበት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከነበረበት ችግር ሳያገግም አሁንም ድረስ በቀጠለው የሰላም እጦት ምክንያት ትምህርት ቤቶች ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነ ነግሮናል፡፡
በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ያነሱት የትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ጉዳቱ ምን ያህል ነው የሚለው ግን ጥናት ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡
ያም ሆነ ይህ ግን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ካሳለፈው እና አሁንም እያሳለፈው ካለ ችግር አገግሞ ጤናማ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዲቀጥል መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሊያግዙን ይገባል ይላሉ፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7








