በመጪው የክረምት ወቅት ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት አንዳንድ አካባበቢዎች ላይ የዝናብ እጥረት ሊከሰት እንደሚችል ተተነበየ።
- 5 hours ago
- 1 min read
ግንቦት 7/2018
በመጪው የክረምት ወቅት ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት አንዳንድ አካባበቢዎች ላይ የዝናብ እጥረት ሊከሰት እንደሚችል ተተነበየ።
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በበልግ ወቅት የነበረውን የአየር ጠባይ ገምግሞ በመጪው የክረምት ወቅት የሚጠበቀውን የአየር ጠባይ ትንበያ መረጃ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
በትንበያው መሰረትም በደቡብና ምስራቅ ትግራይ፤ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ የአፋር ክልል ዞኖች እና ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በታች ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል።
የመካከለኛውና ምዕራብ ትግራይ ዞኖች እና ምዕራብ አማራ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻው ላይ መደበኛና በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ከመደበኛ በታች እንደሚያገኙም ተጠቁሟል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዞኖች፤ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች፤ የጋምቤላ ክልል ዞኖች እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን የሰሜን ምስራቅና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ መደበኛ እና ከመደበኛ በታች ዝናብ እንደሚኖራቸውም ተነግሯል።
በተጨማሪም የመካከለኛውና የደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ በታች ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል ፡፡
በአጠቃላይ ክረምት ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት የምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ መደበኛና ከመደበኛ በላይ እንዲሁም የሰሜን ምዕራብ፤ የሰሜን፤ ሰሜን ምስራቅ፤ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ መደበኛና ከመደበኛ በታች ዝናብ እንደሚያገኙ በትንበያዉ ተመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ገጽታዎች ላይ በመነሳት ተደጋጋሚነት ያለው ከባድ ዝናብ ጋር በተያያዘ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑት ረባዳማ ቦታዎች፤ የወንዝ ዳርቻዎች እና በከተሞች አካባቢ የማህበራዊና የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ሥራዎች ላይ ሊያደርስ የሚችለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመቀነስ እንዲያስችል አስፈላጊዉን የጥንቃቄ ስራ ከወዲሁ በቅንጅት መከናወን እንዳለበትም ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል፡፡
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7

