top of page

ነሀሴ 5 2017 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • Aug 11
  • 2 min read

ፓኪስታን አፍጋኒስታውያን ስደተኞችን በብዛት እያባረረች ነው ተባለ፡፡


የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን(UNHCR) በሕጋዊነትን የተመዘገቡ የአፍጋን ስደተኞች ሳይቀር ከፓኪስታን በብዛት እየተባረሩ ስለመሆኑ አረጋግጫለሁ ማለቱን ዘ ኒው አረብ ፅፏል፡፡


ኮሚሽኑ የአፍጋን ስደተኞች በአሁኑ ወቅት ከፓኪስታን የሚባረሩት በግዴታ እየታሰሩ ነው ብሏል፡፡

ree

በፓኪስታን ከሚኖሩ የአፍጋኒስታን ስደተኞች ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ህጋዊ የስደተኞች ምዝገባ ያደረጉ እንደሆኑ ተጠቅሷል፡፡


የፓኪስታን ሹሞች ግን በህጋዊነት የተመዘገቡትን ሳይቀር በግዴታ ከአገር እያስወጧቸው መሆኑ ተሰምቷል፡፡


የስደተኞች ኮሚሽኑ እንዲህ ዓይነቱ እርምጃ ለአፍጋኒስታን ብቻ ሳይሆን ለመላ ቀጠናው የፀጥታ ስጋት የሚፈጥር ነው ሲል በብርቱ አስጠንቅቋል፡፡


ፓኪስታን የአፍጋኒስታን ጎረቤት አገር ነች፡፡



የጋናው ፕሬዘዳንት ጆን ድራማኒ ማሕማ በቅርቡ ሁለት ሚኒስትሮችን ጨምሮ 8 ሰዎች የሞቱበት የሄሌኮፕተር መከስከስ አደጋ በብርቱ እንዲመረመር እናደርጋለን አሉ፡፡


ሒሊኮፕተሩ ከርዕሰ ከተማዋ አክራ ተነስቶ ወደ አሻንቲ ግዛት በመብረር ላይ በነበረበት ወቅት ጫካ ውስጥ የተከሰከሰው ባለፈው ሳምንት እንደሆነ ቢቢሲ አስታውሷል፡፡


የሄሊኮፕተሩ የበረራ ሂደት መመዝገቢያ /ብላክ ቦክስ/ መገኘቱ ታውቋል፡፡


ማሕማ ግልፅ ማጣራት ይከናወናል ያሉት የበረራ ሂደት መመዝገቢያው መገኘቱን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡


እስካሁን ሒሊኮፕተሩ በምን ምክንያት ሊከሰከስ አንደቻለ የታወቀ ነገር የለም፡፡


የጋና አየር ሀይል ከቅርብ አመታት ወዲህ 3 ተመሳሳይ የሔሊኮፕተር መከስከስ አደጋዎች እንደገጠሙት መረጃው አስታውሷል፡፡



የቀድሞው የቻድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰክሰስ ማስራ የጥላቻ ንግግር አሰራጭተዋል በሚል የ20 አመታት እስር ተፈረደባቸው፡፡


ማስራ እስካለፈው ግንቦት ወር የቻድ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩ ሲሆን የፕሬዘዳንት ማኅማተ ኢድሪስ ዴቢ የፖለቲካ ተቀናቃኝ እና ተቃዋሚ እንደሆኑ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡


በፕሬዘዳንታዊ ምርጫው በማኅማት ኢድሪስ ዴቢ ተሸንፈዋል ከተባሉ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ተባረዋል፡፡


የ20 አመታት እስር የተፈረደባቸው ማስራ ከእስር ቅጣቱ በተጨማሪ እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ መቀጮ እንዲከፍሉ ታዘዋል፡፡


የእሳቸው አባሪ ተባባሪዎች ነበሩ የተባሉ ሌሎች 64 ሰዎችም እያንዳንዳቸው የ20 አመታት የእስር ቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል ተብሏል፡፡


የእነ ማስራ የህግ አማካሪዎች ሒደቱንም ሆነ ፍርዱን የፖለቲካ ውሳኔ ሲሉ መጥራታቸው ተጠቅሷል፡፡



የአውሮፓ አገሮች ከሩሲያ ጋር በጦርነት ላይ ያለችውን ዩክሬይን አለን፣ ከጎንሽ ነን አሏት፡፡


የአውሮፓ ህብረት እና የተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ዩክሬይንን በመደገፍ የጋራ መግለጫ ማውጣታቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡


በጋራ መግለጫው ላይ ከህብረቱ በተጨማሪ የፈረንሳይ ፣ የጀርመን ፣ የጣሊያን ፣ የፖላንድ ፣ የፊንላንድ እና የብሪታንያ መሪዎች ፊርማቸውን አኑረውበታል ተብሏል፡፡


የአውሮፓውያኑ የዩክሬይን መደገፊያ የጋራ መግለጫ ይፋ የሆነው በመጪው አርብ በዩክሬይን የሰላም ጉዳይ የአሜሪካ እና የሩሲያ መሪዎች በአላስካ ይነጋገራሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት ነው፡፡


በአሜሪካ እና በሩሲያ መሪዎች ንግግር ወቅት የግዛት ሽግሽግ ጉዳይ ሊነሳ ይችላል ተብሏል፡፡


የዩክሬይኑ ፕሬዘዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ለሩሲያ ስንዝር መሬት ለመስጠት ፈቃደኞች አይደለንም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page