ነሀሴ 27 2017 - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለ 125,000 ወጣቶች የዲጂታል ስልጠና እድል ማመቻቸቱን ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- Sep 2
- 1 min read
ዲጂታል ስልጠናው ቴክስታርት (Techstart) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ዛሬ ይፋ የተደረገ ነው፡፡
ስልጠናው በኢንተርኔት አማካይነት በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን በመጭዎቹ 3 ዓመታት ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑን በላከልን መግለጫ ተናግሯል፡፡
እንድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸው ወጣቶችን በአማዞን ድረ ገፅ የክህሎት ማዕከል መሰረታዊ የክላወድ ስልጠና እንዲያገኙ ቀጣይነት ያለው የድረ ገፅ አገልግሎት የዲጂታል ስልጠናም አመቻችቻለሁ ብሏል፡፡
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ይህን የማደርገው ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በመደገፍ ቴክኖሎጂ መር የኢኮኖሚ ግቦችን እውን እንዲሆኑ ማህበራዊ ሀላፊነቴን ለመወጣት ነው ብሏል፡፡

በቅርቡ የተመሰረተው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፋውንዴሸን ስልጠናውን በከፍተኛ ውጤት አጠናቅቀው አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው የምስክር ወረቀቶችን መውሰድ ለሚፈልጉ ሰልጣኞችም የመፈተኛ ክፍያዎች እንዲከፍሉላቸው ያመቻቻል ተብሏል፡፡
የፕሮግራሙን ይፋ መሆን አስመልክቶ የኩባንያው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዊምቫን ሄሌፑት አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና ወደ ኢትዮጵያ ያመጣነው የቴክኖሎጂ ኮከቦችን ለማፍራትም በማለም ነው ብለዋል፡፡
የዲጂታል ስልጠና ምዝገባው በቅርቡ ይጀመራል የተባለ ሲሆን ለስልጠናው ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶች በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ማህበራዊ ትስስር ገጾች ይፋ ይደረጋል ተብሏል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments