top of page

ነሀሴ 20 2017 - ኢትዮ ቴሌኮም ወደ የአፍሪካ ሀገሮች ገበያ ውስጥ ለመግባት እቅዴንና ቅድመ ዝግጅቶቼን አጠናቅቄአለሁ አለ

  • sheger1021fm
  • Aug 26
  • 1 min read

ኢትዮ ቴሌኮም ከኢትዮዽያ ገበያ ወጥቼ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ገበያ ውስጥ ለመግባት እቅዴንና ቅድመ ዝግጅቶቼን አጠናቅቄአለሁ አለ።


ኩባንያው በሀገር ውስጥ የዲጅታል አገልግሎት ከመስጠት አልፌ ከኢትዮጵያ ተሻግሬ በ #አፍሪካና ሌሎች ሀገሮችም ገበያ ለመግባት አቅጃለሁ ብሏል።


ይህን ለማድረግም ቅድመ ዝግጅቶችን አጠናቅቄያለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡

ree

ኩባንያው ወደ ሌላ ሀገር ገበያ የምሄደው ገበያውን ለመቀራመት ሳይሆን የዲጅታል መፍትሔዎች ላይ አተኩሬ በምሄድባቸው ሐገሮች መፍትሄ ለማቀበልና ገቢን ለማሳደግ አልሜ ነው ብሏል።


ይህ የተሰማው ዛሬ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የሶስት ዓመት “ቀጣይ አድማስ“ የተሰኘውን የስራ ዘመን የሚፈፅምበትን ስትራቴጂ በተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ ነው፡፡


እነዚህ የትኩረት ስትራቴጂ መንገዶች 6 ምዕራፍ አላቸው ተብሏል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/54y457/


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page