በኢትዮጵያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ላይ የሉም፡፡
- sheger1021fm
- 2 hours ago
- 1 min read
ጥር 22/2018
በኢትዮጵያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ላይ የሉም፡፡
በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተፈጠረ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ያለባቸው ተማሪዎች ሳይሄዱ ቀርተዋል፡፡
ባለፉት አመታት በነበረ አሁንም ድረስ በአንዳንድ አካባቢዎች በቀጠለ የሰላም እጦት ትምህርት ቤቶች በሙሉም ሆነ በከፊል ተጎድተዋል፤ ሰዎች ሰላምን ፍለጋ ቀያቸውን ለቀው ወጥተዋል፡፡
በነዚህ እና በሌሎች ምክንያች ልጆች ከትምህርት ገበታቸው እርቀዋል፡፡
እንደማሳያም የሰላም እጦት ከነበሩባቸው እና አሁንም ድረስ ችግሩ ከቀጠሉባቸው አካባቢዎች መካከል የሆነው አማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን ከጀመረ ወራት ማስቆጠሩ ቢታወቅም እመዘግባለው ብሎ ካቀደው ተማሪ 3 ሚሊየኑን እንዳላገኘ ተናግሯል፡፡
በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት በተፈጠረ ሰላም እጦት ምክንያት በሚሊየን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እርቀው ከርመዋል፡፡
በዚህ ምክንያት ተማሪዎቹ በተከታታይ ሁለት አመት፤ ሶስት አመት እና ከዚያ በላይ ለሚሆን ጊዜ ከመፀሀፍ እና ደብተር እርቀው የቆዩ መኖራቸውን ከክልሎቹ ሰምተናል፡፡
ትውልድን ለማዳን ካስፈለገ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎችን ወደ ገበታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ላይ በትኩረት መስራት ይኖርብናል ተብሏል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ፋሲካ ሙሉወርቅ












Comments