ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ፣ፕሮግራሙ በተተገበረባቸው አካባቢዎች ያሉ የሴት ወጣቶችን ከትምህርት የማቋረጥ ምጣኔን እንዲቀንስ አስችሏል ተባለ።
- sheger1021fm
- 1 hour ago
- 1 min read
ጥር 22/2018
ኤም ኤስ አይ (MSI) ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት አመታት ሲተገበረው የነበረው የወጣቶች የስነ-ተዋልዶና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ፣ፕሮግራሙ በተተገበረባቸው አካባቢዎች ያሉ የሴት ወጣቶችን ከትምህርት የማቋረጥ ምጣኔን እንዲቀንስ አስችሏል ተባለ።
ድርጅቱ በኦሮሚያ ፣በሲዳማ ፣በደቡብ ምዕራብና በደበቡ ክልሎች በካናዳ መንግስት ድጋፍ ሲተገብረው የነበረው የስነ ተዋልዶና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ማጠናቀቂያ ፕሮገራም ተካሂዷል።

በዚህ ፕሮግራም ከ1,000,000 በላይ ወጣቶች ስለ ስነ-ተዋልዶና የቤተሰብ እቅድ አገልገሎት ግንዛቤ እንደተሰጣቸው እንዲሁም ከ300,000 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ አገልግሎት ያገኙበት መሆኑን የድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አበበ ሽብሩ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ፕሮግራሙ ተግባራዊ በተደረገባቸው አራቱ ክልልሎች በስነ ተዋልዶና ቤተሰብ እቅድ አገልገሎት አለማግኘት የተነሳ ሰቶች ላልተፈለገ እርግዝና እንደሚዳረጉ በዚህም ከትምህርታቸው ያቋርጡ እንደነበር ዳሬክተሩ አስታውሰዋል።

በፕሮግራሙ የተነሳ ያልተፈለገ እርግዝና በመቀነሱ የሴቶች የትምህርት ማቋረጥ ምጣኔም እንዲቀንስ አስችሏል ሲሉ አበበ ሽብሩ (ዶ/ር)አስረድተዋል ።
ከዚህ በተጨማሪም የእናቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥማቸው ሞት እንዲቀንስ ማስቻሉን ፣የስነ ተዋልዶና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተደራሽነት እንዲያድግ ፕሮግራሙ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ሰምተናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ምህረት ስዩም












Comments