top of page

ነሀሴ 2 2017 - ቢሾፍቱ አካባቢ በሚገኙ የአበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ እርሻዎች ላይ ከባድ ዝናብ ከፍ ያለ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል

  • sheger1021fm
  • Aug 8
  • 1 min read

በቢሾፍቱ አካባቢ በሚገኙ ሰባት የአበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ እርሻዎች ላይ ከቀናት በፊት ከባድ ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ ከፍ ያለ ጉዳት ማድረሱ ተነገረ።


ጉዳት ከደረሰባቸው እርሻዎች የተወሰኑት ወደ ቀደመ ሁኔታቸው ለመመለስ ረዘም ያለ ጊዜ እና ከፍተኛ ገንዘብ ሊጠይቃቸው ይችላል ተብሏል።


ባለፈው ሰኞ #ቢሾፍቱ አካባቢ በሚገኙ ሰባት የአበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ እርሻዎች ላይ ከባድ ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ የጣለው #ዝናብ ከፍ ያለ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል።


ዝናቡ በማምረቻ ሼዶች ፤ በአበባ ምርቶች እና በላብላቶሪዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት ማድረሱን ሠምተናል።


ሬንቦ ከለርስ የአበባ እርሻ ብቻ ስምንት ሄክታር ላይ የነበረ ምርት ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጪ እንደሆነበት ነግሮናል።


ያሲን ለገሰ የአበባ እርሻ ልማትም በተመሳሳይ በዚሁ ከባድ ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ ከፍ ያለ እንደገጠመው ሠምተናል።


የአበባ እርሻው ስራ አስኪያጅ አቶ ሃይልዬ ንጌሴ እንደነገሩን ዳግም ወደ ምርት ለመመለስ እስከ ስምንት ወር ሊጠይቃቸው ይችላል። አሁን ላይ የተቀዳደዱ የማምረቻ ሼዶችን ፕላስቲኮች በሌሎች የመተካት እና የወዳደቁ ብረቶችን በድጋሚ የመትከል ስራ እያከናወኑ እንደሚገኙ አቶ ሃይልዬ ነግረውናል።


ጉዳት የደረሰባቸውን የአበባ እርሻዎች ወደ ቀደመ ይዞታቸው ለመመለስ ከፍ ያለ ወጪ እንደሚጠይቅ የተናገሩት ፤ የሬንቦ ከለርስ የአበባ እርሻ ስራ አስኪያጅ አቶ ይበልጣል እርቅይሁን በበኩላቸው ጉዳዩ የመንግስትም ዕገዛ የሚያስፈልገው እንደሆነ አክለዋል።


ከመንግስት ሊደረግ የሚገባውን ድጋፍ በተመለከተ በኢትዮጵያ የአበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች እና ላኪዎች ማህበር በኩል ፤ ጥናት ላይ የተመሰረተ ጥያቄ ለማቅረብ እየሰራን ነው ሲሉም ሁለቱ የስራ ሃላፊዎች ነግረውናል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…


ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page