top of page

ነሀሴ 1 2017 - በኢትዮጵያ ከ71 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ጤናማ ምግብ ማግኘት እንደማይችሉ መረጃዎች ያሳያሉ

  • sheger1021fm
  • Aug 7
  • 1 min read

በኢትዮጵያ ከ71 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ጤናማ ምግብ ማግኘት እንደማይችሉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡


የሥነ ምግብ ባለሞያዎች እንደሚሉት ከሆነ በኢትዮጵያ ከጤናማ ምግብ በተጨማሪ ሰዎች በቀን ውስጥ ማግኘት የሚገባቸውን የካሎሪ መጠን እያገኙ እንዳልሆነ ተናግረዋል።


አንድ ህጻን በቀን ውስጥ እስከ 1,600 ካሎሪ የሚያስፈልገው ሲሆን አዋቂዎች ደግሞ እስከ 2,500 ካሎሪ እንደሚያስፈልጋቸው ሰምተናል፡፡


ሆኖም በኢትዮጵያ ህፃናትም ይሁኑ አዋቂዎች ይህን ያህል ካሎሪ መጠን ያለው ምግብ ማግኘት እየቻሉ አይደለም ተብሏል፡፡

ይህ ባልሆነበት ስለጤናማ ምግብ ለማሰብ እጅግ አስቸጋሪ ነው ሲሉ የነገሩን በዓለም አቀፉ የምግብ ምርምር ፖሊሲ ተመራማሪ ሳይንቲስት የሆኑት ታደሰ ዘርፉ(ዶ/ር) ናቸው፡፡


ሰዎች ስለ ጠገቡ ብቻ ጤናማ ምግብ አግኝተዋል ማለት እንዳልሆነ ያነሱት ተመራማሪው ስለ ጤናማ ምግብና ከእሱ ጋር ተያይዘው መታየት ስላለባቸው ጉዳዮች አስረድተዋል፡፡


በአጠቃላይ በዓለም ላይ 295 ሚሊዮን ሰዎች በከፋ ምግብ ውስጥ እንደሚገኙ በተባበሩት መንግታት ድርጅት የእርሻና የምግብ ፕሮግራም ፋኦ ያወጣው ሪፖርት ይናገራል፡፡


እዚህ ቁጥር ውስጥ ኢትዮጵያን ትገኝበታለች ለዚህ እንደ ምክንያት ይነሳል ያሉትንና በሪፖርቱ የተመለከቱትን ተመራማሪውን ነግረውናል፡፡


በዚህም የእርስ በርስ ግጭት፣ የኮቪድ ወረርሽኝ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page