top of page

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ደራሲና ፀሀፊ ዲናው መንግስቱ በኒውዮርክ የሚገኘውን ፔን አሜሪካን በፕሬዘዳንትነት እንዲመሩ ተመረጡ።

  • sheger1021fm
  • 9 minutes ago
  • 2 min read

ታህሳስ 11/2018

 

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ደራሲና ፀሀፊ ዲናው መንግስቱ በኒውዮርክ የሚገኘውን ፔን አሜሪካን በፕሬዘዳንትነት እንዲመሩ ተመረጡ።

 

ከትናንት በስቲያ እሮብ የፔን አሜሪካ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ በተደረገ ምርጫ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዲናው መንግስቱ ድርጅቱን በፕሬዘዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

 

የ103 ዓመት እድሜ ያለው ታዋቂው ተቋም "ፔን አሜሪካ" ዋና መቀመጫውን በኒውዮርክ ያደረገና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡

 

ተግባሩም ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን መደገፍ ፣ ለስነ ፅሁፍ እድገትና ነፃነት መታገል፣እንዲሁም በአጠቃላይ በአለም ዙሪያ ሰብአዊ መብት እንዲከበር መስራት መሆኑ ይነገራል፡፡

 

ፔን በመላው አለም ለተመሳሳይ ዓላማ የቆሙ ከ100 በላይ ድርጅቶችን የያዘና በጋራ አሰባሳቢ ጥላው ፔን ኢንተርናሽናል በሚል መጠሪያ የሚታወቅ ትልቅ ተቋም ነው፡፡

ree

በአሜሪካ ኒውዮርክ ዋና ቢሮውን ያደረገው ፔን አሜሪካም በሎስ አንጀለስ ፣ ዋሽንግተን ዲሲ እና በፍሎሪዳ ተጨማሪ ቢሮዎች አሉት፡፡

 

ፔን አሜሪካ በተጨማሪም በመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ፣ የደራሲያንና ፀሐፊያን ደህንነት ፣ በከፍተኛ ት/ት ተቋማት ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ፣ በድረ ገፅ ጥቃት፣እንዲሁም የኪነ ጥበብ ስራዎች ነፃነት ዙሪያ በስፋት የሚሰራ እና የሚታገል እንደሆነ ይነገራል፡፡

 

ይህንን ግዙፍ ተቋም በፕሬዘዳንትነት እንዲመሩ ነው ትውልድ ኢትዮጵያዊው ፀሐፊና ደራሲ ዲናው መንግስቱ የተመረጡት።

ዲናው መንግስቱ በኒውዮርክ የሚገኘውና የኪነ ጥበብ ኮሌጅ የሆነው ባርድ ኮሌጅ የሪትን አርት ፕሮግራም ዳይሬክተር ሆነውም ይሰራሉ።

 

ኢትዮጵያ አሜሪካዊው ደራሲ ዲናው መንግስቱ ትውልዳቸው በአዲስ አበባ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኙ መፅሐፍትን ለንባብ አብቅተዋል።

 

ሰም ዋን ላይክ አስ፣ ኦል አወር ኔምስ፣ ሀው ቱ ሪድ ዘ ኤይር፣ እንዲሁም ዘ ቢውቲፉል ቲንግስ ዛት ሄቨን ቢርስ መፅሐፎች ብዙ የተነበቡና እውቅና የተሰጣቸው ናቸው፡፡

 

እንዲሁም በአሜሪካ ታዋቂ በሆነው ጂን መፅሔት ላይ ስለ ሰሜናዊ ዩጋንዳ ግጭት ፣ እንዲሁም በሌላኛው የአሜሪካ ወርሃዊ መፅሔት ሮሊንግ ስቶን ስለ ሱዳኑ የዳርፉር ጦርነት ባቀረቧቸው ፅሁፎችም ይታወቃሉ።

 

ree

በእነዚህና በሌሎችም በርካታ ስራዎች የ47 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ደራሲና ፀሀፊ ዲናው መንግስቱ የተለያየ አለም አቀፍ እውቅናን አግኝተዋል።

 

የታዋቂው ፔን አሜሪካ ተቋም ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውንም ኒውዮርክ ታይምስን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበውታል፡፡

 

ከዲናው መንግስቱ ስራዎች አንዱ የሆነውና ባለፈው አመት ለንባብ የበቃው ሰም ዋን ላይክ አስ መፅሐፍ በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የአመቱ ምርጭ 10 መፅሐፍት ዝርዝር ውስጥ ተካቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

 

ይህ መፅሐፍ ከእንግሊዘኛ በተጨማሪ ከ15 በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉሞም ለንባብ በቅቷል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..

 

ቴዎድሮስ ወርቁ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Recent Posts

See All
ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ 

ታህሳስ 11/2018   ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡   የአማራ ክልል የአደጋ ስጋት መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ መልስ ለመስጠት አልፈቀደም።   ከመንግስት የሚቀርበውን ድጋፍ ለተፈናቃዮች የሚያከፋፍለውና ሌሎች ስራዎችን የሚሰራው በመንግስት የተቋቋመ ኮሚ

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page