top of page

ቴክኖሎጂውን ተገን አድርገው ‘'የዲጂታል ዘመን ቀማኞች’ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።

  • 2 hours ago
  • 2 min read

መጋቢት 16/2018


ያለንበት የዲጂታሉ ዓለም የሰውን ልፋት በመጋራት ትልቅ እፎይታን አስገኝቷል፡፡


ድካምን መቀነሱ፣ ኑሮን ማቅለሉ፣ የራቀ የመሰለውን አቅርቦ ፣ ሁሉንም በቀላሉ መረጃን በእጁ መዳፍ፣ ግብይትን በጣቶቻቹ ንክኪ እንዲሆን እድልን ፈጥሯል።

ነገር ግን ቴክኖሎጂውን ተገን አድርገው ‘የዲጂታል ዘመን ቀማኞች’ ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።


በዚህ በዲጅታል አለሙ የማታለያ ዘርፉ ብዙ ነዉ፡፡


በየጊዜው አዳዲስ የማጭበርበሪ መላዎች ይሰማሉ። አታላዮች የሚዘረጉት መረብ እንደየሰው ማንነት ይለያያል።


ለወጣቱ ያልሰራህበት ትርፍ፣ ለአዛውንቱ የልጅነት ፍቅርና ርህራሄ፣ ለተቸገረው ፈጣን ብድር ሌላም ሌላም ብዙ ነገሮች አማራጭ ሆነዉ ይቀርባሉ፡፡


በዚህ መንገድ አሁን አሁን ላይ ተጭበረበርኩ፣ ይህን ገንዘብ ተወሰደብኝ፣ ለአመታት ኳትኜ ያጠራቀምኩትን ጥሪት ተነጠቅሁኝ የሚሉ ሰዎችም ቁጥራቸው ብዙ ነው ።


በእርግጥ አጭበርባሪዎች የተለያዩ ዘዴዎችን ተጠቅመዉ እንደሚያታልሉ በባንክም፣ በቴሌኮምም ፣ በፖሊም የማስጠንቀቂያ መልክቶች ይደርሳሉ።


ግን አሁንም የሚጭበረበሩ ሰዎች ቁጥር ብዙ ነው።

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የስነ ወንጅል እና የስነ ልቦና አስተማሪ የሆኑት ዋ/ኢ/ር ጉግሳ ግብረግዚቤር ብዙዎች ማጭበርበርን ከስግብግብነት ጋር ብቻ ያያይዙታል።


ያልሰሩበትን ለማግኘት መጓጓት’ ለአታላዩ ዋነኛ መግቢያ በር እንደሆነ ባይካድም፣ ነገሩ ግን አታላዮች የሚጠቀሙት መሣሪያ ‘ቴክኖሎጂን’ ሳይሆን ‘የሰውን ልጅ ስነ-ልቦናዊ ድክመት’ ነዉ ይላሉ።

በተለይም "ከባንክ፣ ከቴሌ ወይም ከታወቁ ድርጅቶች የተደወለ በማስመስል የታወቁና የተከበሩና ሰዎችን ፣ የሀይማኖት አባት ፣ ፖሊስ ፣ ባለስልጣን በመምሰል በማዋከብ ፣ የማሰብና የማገናዘብ እድልን በመንፈግ ሰው በደመ-ነፍስ ውሳኔ ላይ እንዲርስ ማድረግ አታላዮች ከሚጠቀሙባቸዉ ዘዴዎች መካከል ናቸዉ ይላሉ፡፡

አታላዮች የሚመጡበት መንገድ የሚገመት ላይሆን ይችላል፡፡ በየጊዜው የሚከሰቱበት መላም ይለያያል። ነገሮችን ከወቅታዊ ነገሮች ጋር አገናኝተው እውነት የሚመስልን ሀሳብ ያቀርባሉ።


ደግሞ አሁን ላይ ሁሉም የሚከወነው በድጂታል ሆኗል።


ከዚህ ርቆ ከቴክኖሎጅው ተጣልቶ ለመኖርም የሚቻል አይደለም።


ታዲያ መፍትሄው ምንድን ነው? የስነ-ወንጀል አስተማሪው ለተነገረው፣ ለተባለው ሁሉ ሳይጓጉ በእርጋታ አመዛዝኖ መወሰን ፣ ራስን ከዲጅታሉ አለም ጮሌዎች ማዳኛው መንገድ ስለመሆኑም ዋ/ኢ/ሩ መክረዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….



ገዛ ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page