top of page

ታሪክን የኋሊት - መስከረም 20 2018

  • sheger1021fm
  • Sep 30
  • 2 min read
ree

የአሜሪካ ሴቶች የመምረጥ መብታቸውን እንዲከበርላቸው ፣ ፕሬዝዳንት ዊድሮው ዊልሰን በይፋ አቋማቸውን የገለፁት ፣ በ1911 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡


ፕሬዝዳንቱ፣ ሴቶችን የሚደግፍ ንግግር ማድረጋቸውና አቋም መያዛቸው ለአመታት የአሜሪካ ሴቶች ፣ለእኩልነት የመብት ተጠቃሚነት ለሚያደርጉት ትግል ከፍ ያለ ጥቅም ነበረው፡፡


የሴቶችን የመምረጥ መብት፣ የተወካዮች ምክር ቤት በድምፅ ብልጫ ቢያሳልፈውም ሴኔቱ ግን ባለመስማማቱ ታግዶ ቆየ፡፡


19ኛው የሕገ መንግስት ማሻሻያ፣ የሴቶችን የመምረጥ መብት ቢደግፍም፣ በሴኔቱ ደጋፊ ባለማግኘቱ የተከለከለ መብት ሆነ፡፡


መብታቸው እንዲከበር፣ በሚታገሉና ሰልፍ የሚወጡ ሴቶች ታሰሩ፡፡


በርግጥ፣ በአንዳንድ ግዛቶች መለስተኛ የመምረጥ መብት እንዲለማመዱ ተደርጓል፡፡



ሴቶች የመምረጥ መብታቸው እንዲከበር ያነሱት ጥያቄ መልስ ሳያገኝ ለ70 አመታት ቆይቷል፡፡


በ1840ዎቹ መጨረሻ ፣ኤልሳቤጥ ኪዲይና ሉክሪሽያኑ፣ በመላ አሜሪካ ሴቶች ለመብታቸው እንዲታገሉ አደራጇቸው፡፡


የሴቶች የመምረጥ መብት ይከበር በሚል መሪ ቃል ድምፃቸውን አሰሙ፡፡


ታላላቅ ሰላማዊ ሰልፎችን አደረጉ፡፡


የፀጥታ ሀይሎችም አስሩዋቸው ፤ ደበደቧቸው፡፡


መንግስት ባሰራቸውና ባስፈራራቸው መጠን፣ የበለጠ እየተደራጁ ትግላቸውን ጠነከሩ፡፡


በአንደኛው የአለም ጦርነት፣ ተሳትፏቸው ፣ የአሜሪካ ሴቶች ጉልህ ስለነበር፣ ፕሬዘዳንት ዊድሮ ዊልሰን መስዋዕትነት ለከፈሉት ሴቶች፣ የመምረጥ መብታቸው እንዴት ይከለከላል ብለው በይፋ ተሟገቱ፡፡


“በዚህ ጦርነት ሴቶችን አሳትፈናል ታዲያ ለመስዋዕትነት እየጠራን፣ የመምረጥ መብታቸውን መከልከል ይገባናል ወይ? አሉ፡፡


ዊድሮ ዊልስን ጠንካራ የድጋፍ ንግግር ቢያደርጉም፣ ሴኔቱ አልፈቀደም፡፡


የሴቶች የመምረጥ መብት እንዲከበርና ሌላ ሁለት አመት ወስዷል፡፡


ኮላራዶን፣ ናቫዳን ካንሳስን ጨምሮ ግዛቶች፣ የሴቶችን የመመረጥ መብት ቀድመው አስከብረዋል፡፡


ግን የፌዴራሉ መንግስት ህግ አላደረገውም፡፡


በ1913 ዓ.ም፣ የሴቶች የመምረጥ መብት ቢደነገግም፣ የተወላጆቹ አሜሪካኖች ሴቶች መብት ለመከበር፣ ሌላ አራት አመት ወስዷል፡፡


የእስያ ተወላጅነት ያላቸው ሴቶችም ፣ የመምረጥ መብታቸው 13 ዓመታት ዘግይተው ነው የተከበረላቸው፡፡


የፕሬዘዳንት ዊድሮ ዊልሰን የድጋፍ ንግግር፣ ረቂቁን ለማሳለፍ ይረዳል ተብሎ በታመነበትም ለጊዜው አልተሳካም፡፡


ከአመት በኋላ፣ በነሐሴ 1912 ዓ.ም የአሜሪካ ሴቶች የመምረጥ መብት መከበሩ፣ ህግ ሆነ ፀደቀ፡፡


ፕሬዝዳንት ዊልሰን ፣የሴቶችን የመምረጥ መብት ደግፈው ጠንካራ ንግግር ካደረጉ 105 ዓመት ሆነ፡፡


እሸቴ አሰፋ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page