top of page

ታህሳስ 4፣ 2015- የኩዌት ፓርላማ የተጭበረበረ የግብፅ ዩኒቨርስቲዎች ዲግሪዎችን የያዙ ከ140 በላይ ሰዎች ላይ ደረስኩባቸው አለ


የኩዌት ፓርላማ የተጭበረበረ የግብፅ ዩኒቨርስቲዎች ዲግሪዎችን የያዙ ከ140 በላይ ሰዎች ላይ ደረስኩባቸው አለ፡፡


የፓርላማው የትምህርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን እያጣራው መሆኑን ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡


የዚህ ሐሰተኛ ዲግሪ አሰራጮች እነማን እንደሆኑ ክትትሉን አበርትቶታል ተብሏል፡፡


በዚሁ ጉዳይ መነሻ ነዋሪነቱ በኩዌት የሆነ ግብፃዊ ተይዞ መታሰሩ ታውቋል፡፡

የግለሰቡ መያዝ የዚህን የወንጀል መረብ ጥልፍልፎች ለመፍታት ፍንጭ እንደሚሰጥ ታምኖበታል ተብሏል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


bottom of page