top of page

ታህሳስ 17፣ 2015- ሶማሊያ ውስጥ በአልሸባብ ፅንፈኛ ቡድን ታግተው የቆዩ 14 ኢራናዊያን ዓሣ አስጋሪዎች ተለቀው አገራቸው መግባታቸው ተሰማ


ሶማሊያ ውስጥ በአልሸባብ ፅንፈኛ ቡድን ታግተው የቆዩ 14 ኢራናዊያን ዓሣ አስጋሪዎች ተለቀው አገራቸው መግባታቸው ተሰማ፡፡


ኢራናውያኑ ዓሣ አስጋሪዎች ለ8 ዓመታት በአልሸባብ ታግተው መቆየታቸው ታስም የወሬ ድርጅት አስታውሷል፡፡


ዓሣ አስጋሪዎቹ የተለቀቁት የኢራን መንግስት ባደረገው ብርቱ ድርድር ነው ተብሏል፡፡


ከ8 ዓመታት በፊት በኢራናውያኑ ዓሣ አስጋሪዎች ላይ እገታው ተፈፅሞቸው የነበረው በአለም አቀፍ የባህር መስመር ላይ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡


የሶማሊያ መንግስት ጦር ከአልሸባብ ፅንፈኛ ቡድን ጋር ሲዋጋ ከ15 አመታት በላይ ሆኗታል፡፡


በአሁኑ ወቅትም ፅንፈኛውን ቡድን ለመደምሰስ መጠነ ሰፊ ዘመቻ እያደረገ መሆኑ ይነገራል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page