top of page

ታህሳስ 12፣ 2015- በአፍጋኒስታን የታሊባኖች አስተዳደር በአገሪቱ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ሴቶች እንዳይማሩ ከለከለ


በአፍጋኒስታን የታሊባኖች አስተዳደር በአገሪቱ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ሴቶች እንዳይማሩ ከለከለ፡፡


ክልከላው ያለ ምንም መዘግየት በአገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ስራ ላይ እንደሚውል የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ መናገራቸው ሻይን ድረ ገፅ ፅፏል፡፡


ባለፈው አመት ሴት ልጆች በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዳይማሩ መከልከላቸው ዘገባው አስታውሷል፡፡


የአሁኑ እርምጃ የአፍጋኒስታን ሴት የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎችን በእጅጉ እያሳዘነ ነው ተብሏል፡፡


ሴቶቹ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ውሳኔው የወደፊት ተስፋችንን አጨልሞብናል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


ጉዳዩ በአለም አቀፍ ደረጃም ውግዘት እየገጠመው ነው ተብሏል፡፡


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍጋኒስታን ሴቶች በዩኒቨርስቲዎች እንዳይማሩ መከልከላቸውን በፅኑ አውግዞታል ተብሏል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

bottom of page