በየቤት ሰራተኞች እና በአሰሪዎች መካከል የሚፈጠሩት መቃቃር፣ አለመተማመኖች እና ችግሮችን ለመፍታት
- 2 hours ago
- 1 min read
ሰኔ 5/2018
በየቤት ሰራተኞች እና በአሰሪዎች መካከል የሚኖርን አሰራር ህጋዊ ለማድረግ አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ እንደሆነ ይታወቃል።
ደንቡ እየተዘጋጀ ያለው በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሲሆን ከሁለቱም ወገን ሊፈጠር የሚችልን አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጥቃቶችን ለመከላከል ያስችላል ተብሎ ታምኖበታል፡፡
ይህንን ደንብ ማውጣት አንዱ መሰራት ያለበት ስራ ቢሆንም የቤት ሰራተኞች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት እና አሰሪዎችም እነሱን ከመቅጠራቸው አስቀድሞ ስልጠና ቢወስዱ መልካም እንደሚሆን በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ አንድ ባለሙያ ያስረዳሉ፡፡

በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሁለቱም ወገን ያለው መቃቃር፣ አለመተማመኖች እና ችግሮች ክፍተቶቹ እየሰፉ መጥተዋል ያሉት ባለሙያው ህጉን ወረቀት ላይ ከማስፈር ባለፈ የሞያ ልምድ፣ ሰራተኞች ካሰሪዎቻቸው ጋር ስለሚደርጉት ተግባቦት እና ስለሌሎች ጉዳዮች ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል፡፡
ነገር ግን አሁንም ህጉ ላይ ብቻ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራ ከሆነ እና ሰራተኞች ከአሰሪዎቻቸው ጋር ሊኖራቸው ስለሚገባ ግንኙነት፣ የአቅም ግንባታ፣ የሞያ ብቃት ምንም ዓይነት ግንዛቤ ካልያዙ ችግሩ ውሃ ቅዳ ውሀ መልስ እንደሚሆንም ያስረዳሉ።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i

