top of page

ባንኮች ከጡረታ መዋጮ የአገልግሎት ክፍያ በሚል መቁረጥ አይችሉም ተባለ።

  • Dec 22, 2025
  • 1 min read

ታህሳስ 13/2018


ባንኮች ከጡረታ መዋጮ የአገልግሎት ክፍያ በሚል መቁረጥ አይችሉም ተባለ።


አንዳንድ ባንኮች የጡረታ ክፍያ ለተጠቃሚዎች ሲክፍሉ የአገልግሎት ክፍያ በሚል እንደሚቆርጡ ተነግሯል።


የአገልግሎት ክፍያውን እየቆረጡ ያሉት ብሄራዊ ባንክ መመሪያ አውጥቷል በሚል እንደሆነ ተጠቅሷል።

በ2014 የወጣው የጡረታ አዋጅ ግን ከጡረታ መዋጮ ገንዘብ ላይ ቀንሶ ለአገልግሎት ክፍያ፣ ለገንዘብ ማስተላለፊያ እያሉ መጠቀም እንደማይቻል ይደነግጋል ተብሏል።


ብሄራዊ ባንክ አወጣው የተባለው መመሪያ ከአዋጁ በላይ ሊሆን ስለማይችል ግን ተግባሩ ሊቆም ይገባል ሲሉ የአስተዳደሩ የህግ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሢሣይ አሳስበዋል።


የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በጡረታ አዋጁ ዙሪያ ከሚመለከታቸው ጋር በኢሊሊ ሆቴል እያካሄደ ነው።


ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Recent Posts

See All
በኢትዮጵያ የንግዱን ማህበረሰብ እየገጠሙ ካሉ ችግሮች 40 በመቶ ያህሉ ከገንዘብ አቅርቦት ጋር የተገናኙ ናቸው ተባለ ።

መጋቢት 3/2018 በኢትዮጵያ የንግዱን ማህበረሰብ እየገጠሙ ካሉ ችግሮች 40 በመቶ ያህሉ ከገንዘብ አቅርቦት ጋር የተገናኙ ናቸው ተባለ ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ 2 ሚሊየን የሚጠጉ ጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ኢንዱስትሪ ተቋማት እንዳሉ ተነግሯል። የእነዚህ ኢንዱስትሪ ባለቤቶችና ኢ-መደበኛ በሆኑ ሌሎች ንግ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page